banner

የጥምቀት ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከል ሊካሄድ ነው!

#FastMereja I ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠ እውቅና እና ፍቃድ መሰረት የአዲስ አመት፣ የመስቀል፣ የገና፣ የጥምቀት፣ የፋሲካ እና የዳግማይ ትንሳኤ ሀይማኖታዊ በዓላት ላይ ትኩረቱን በማድረግ የንግድ ትርኢት እና ባዛሩን ከመንፈሳዊ አውደ ምህረት መርሃ ግብሮች ጋር በማጣመር የሚተገበርው «የተዋሕዶ ኤክስፖ» ፕሮጀክት አካል የሆነው የጥምቀት ኤክስፖ የንግድ ትርኢት እና ባዛር በከተማችን አዲስ አበባ በኤግዚቢሽን ማዕከል ሊካሄድ ነው።

ማርኮናል ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከኢኦተቤ ጠቅላይ ቤተክህነት ፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ከኬብሮን የዝግጅት አጋፋሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር የሚዘጋጁት ይህ ኤክስፖ ፣ ዜጎችን በአንድ ማዕቀፍ በማድረግ በሰከነ መንፈሳዊ ስነ ምግባር ባለሙ እና ታዓማኝነት በሰፈነበት የምርት እና የአገልግሎት አቅርቦት እና ለማህበረሰቦች በየ ደረጃው የስራ እድል የመፍጠር እና የሀገር ገጽታ የሆኑን በዓላቶቻችንን ለቱሪስት መስህብ በሚሆን ደረጃ በመስራት አለም አቀፍ ግንኙነትን መፍጠር የሚያስችል እንዲሆን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልዖል።

«አብሮነት ለእድገት›› በሚል መሪ ቃል የሚሰናዳው ይህ ‹‹ጥምቀት ኤክስፖ›› የንግድ ትርኢት እና ባዛር ከጥር 03 እስከ ጥር 09 ቀን 2017 ዓ/ ም ለተከታታይ 7 ቀናት በኤግዚቢሽን ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል።

በዚህ ልዩ ኤክስፖ የምሽቱ መርሃ ግብር ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ማህበራት፣ ህብረ ዘማሪያን እንዲሁም በርካታ ዘማሪያን እና የኪኑ ጥበብ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት 17 ታላላቅ የዝማሬ እና መንፈሳዊ የኪነ ጥበብ ጉባኤዎች የሚኖሩ ሲሆን ከ42 በላይ የሆኑ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ አመሻሽ 10፡00 ሰዓት ለተከታታይ 5 ቀናት መንፈሳዊ ሽልማት የሚያስገኙ የጥያቄ እና መልስ እንዲሁም የሥኑ ግጥም ውድድር የሚያካሒዱ ይሆናል።



Leave a Comment