0
#FastMereja I አራት የአማርኛ ፊልሞች ማለትም ጭረት፣ እጅ አልሰጥም፣ ወጣት በ97 እና ለፍትህ የተሰኙ ፊልሞች በቴሌ ቲቪ ለእይታ ሊቀርቡ እንደሆነ ዛሬ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል በተካሄደ የፊርማ ስነ ስርዓት ተገልጿል።
ቴሌ ቲቪ ለመዝናኛ ኢንደስትሪው በተለይም ደግሞ ለፊልም ኢንደስትሪው ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረና አዳዲስ ፊልሞችን ብቻ ሳይሆን ለአጭር ጊዜ ታይተው ከሲኒማ የወረዱ ብዙ የተደከመባቸውን ፊልሞችን እንደገና ለሕዝብ እንዲቀርቡ ሁነኛ አማራጭ ሆኖ መገኘቱን የኤግላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ መሥራችና ዋና ሥራ አሥኪያጅ አቶ በእርሱፈቃድ ጌታቸው ተናግሯል በተጨማሪም በቅርቡ ቴሌ ቲቪ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እና የተለያዩ ሽልማቶችን ለተመልካች እንደሚሰጥ ገልጸዋል ።
በዚህ ቴሌ ቲቪ የሚባል አፕ የተመረጡ ደረጃቸውን የጠበቁ አማርኛ ፊልሞችን ለእይታ የሚያበቃ ሲሆን እነዚህን ፊልሞች ለማየት በሀገር ውስጥ በቴሌ ብር በውጭ ሀገር፣ በማስተር ካርድ፣ ቪዛ እና በአሜሪካን ኤክስፕረስ የክፍያ አማራጮች ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል፡፡




