banner

ለገና በዓል ምርት እጥረት እንዳይከሰት የገበያ ትስስር ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ

ለገና በዓል ምርት እጥረት እንዳይከሰት የገበያ ትስስር ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በዓሉን ለማክበር የሚያስችል ምቹ ሁኔታና ህብረተሰቡ የተረጋጋ ግብይት ስርዓት ኖሮት የምርትን በአግባቡ ሸምቶ በዓሉን እንዲያከብር ዝግጅት መደረጉን የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩሪያ ገለፁ፡፡

እንደ ኃላፊዋ ገለፃ የክልሉ በመንግስት ድጎማ የቀረበውን 370,000 ሊትር የምግብ ዘይት በከተማ አስተዳደርና በወረዳዎች የተደለደለውን ኮታ መሠረት በማድረግ በሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበራት አማካይነት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡

በክልሉ ከዚህ በፊት የነበረውን የእሁድ ገበያ (Sunday Market) የመሸጫ ቦታዎችን ከ64 ወደ 68 በማሳደግ ሸማቹንና አምራቹን ማህበረሰብ በምርት አቅርቦት፣ በዋጋና በጥራት በቀጥታ ተገናኝተው መገበያየት የሚችሉበትን የአሰራር ሥርዓት ተዘርግቶ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በክልሉ ከሕብረት ሥራ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበራት የሌማት ቱሩፋት ውጤቶችን በዩኔኖች እና በግል ጅምላ አከፋፋዮች በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘገጀው ባዛርና ኢግዚብሽን የኢንዱስትሪ ምርቶች በተጨማሪ የግብርና ምርቶችም የተሻለ ዋጋ እንዲቀርብ ማደረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ የቁም እንስሳት ግብይት የሚፈፀምበት በሀዋሳ ከተማ የቱላ ክፍለ/ከተማን ቅኝት አድርገናል ያሉት ኋላፊዋ እንደተመለከትነውም በቂ የቁም እንስሳት በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡንም መመልከታቸው ገልፃዋል፡፡

በቱላ ገበያም አነስተኛ ወይፈን ከ20ሺህ እስከ 30ሺህ፤ መካከለኛ በሬ 40ሺህ እስከ 75ሺህ እና ከፍተኛ በሬ ከ80ሺህ እስከ 110ሺህ እየተተሸጠ መሆኑን የሰንጋ ነጋዴዎች ማሳወቃቸውም ተገልፆል፡፡

ሕብረተሰቡ በበዓል ወቅት ግብይት በሚፈፀምበት ጊዜ መጠቀሚያ ጊዜ ያፈባቸው ምርቶችን፤ ከባዕድ ጋር የተደባለቁ፣ ጥራት ደረጃቸው የወረዱና ለሰው ጤንነትና ደህንነት የሚያሰጉ ምንጫቸው ያልታወቁ ምርቶች ከመሸመት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኋላፊዋ አሳስበዋል፡፡

በግብይት ወቅት የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከል ከክልል እስከ ከተማ አስተዳደርና ወረዳ ድረስ የዘለቀ የተቋቋመ የዋጋ ማረጋጋት ግብረ-ኃይልና ለፖሊስ አካላት መኖራቸውን የገለፁት ወ/ሮ ሰላማዊት እንዲህ አይነት ህገ-ወጥ ችግር የገጠማቸው አካላት በቢሮ ነፃ ስልክ መስመር 63-79 ጥቆማ በመስጠት ከሕገ-ወጦች ሕብረተሰቡ እራሱን እንዲከላከልና መብቱን እንዲያስጠብቅ አሳስበዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሠላማዊት መኩሪያ ከፊት ለፊታችን ለሚከበረው የገና በዓል ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን አደረሳችሁ ብልዋል። ኃላፊዋ አክለውም በዓሉ የሰላም፤የፍቅርና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡





1 comment

Tsegaab Dawit January 5, 2025 - 5:46 pm

ሰላም አንደኛ 👏

Reply

Leave a Comment