የኦቪድ ሆሊዲንግ ኩባንያዎች እህት ድርጅት የሆነው ኦቪድ ሪል ስቴት ለክቡራን ደንበኞቹ እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን 2017 ዓ.ሞ ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ ይላል።
ኦቪድ ሪል ስቴት በዚሁ አጋጣሚ ለክቡራን ደንበኞቻችን እና በአጠቃላይ ለማህበረሰባችን የሚከተለውን መረጃ ለማጋራት ይወዳል።
ኦቪድ ሬል ስቴት በሀሰት መልካም ስሙና ዝናው ላይ ጉዳት ለማድረስ እየተንቀሳቀሱ ባሉ አካለት ላይ ጉዳያቸው በሕግ እንዲታይ ለማደረግ ክትትል እያደረገ ነው !
ደርጅታችን ኦቪድ ሆን ብለውና በቸልተኝነት ሀሰተኛ መረጃ ላቀረቡ አካላት ስህተታቸውን እንዲያርሙ በዝርዝር ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ የጀመረውን የክስ ሒደት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ድርጅታችን ኦቪድ ሪል ስቴት በኦቪድ ሆልዲንግ ስር ካሉ በርካታ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን በሪል ስቴት ዘርፍ የተሰማራ ስኬታማ ተቋም ነው፡፡ ድርጅታችን ኦቪድ ሬል ስቴት በአገራችን በተለይ በከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመሰረተ የግንባታ ስልትን በመንደፍ በዋጋ፣ በጥራት እና በፍጥነት በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ገንብቶ በርከት ያለ የማሕበረሰብ ከፍልን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡
ወደ ተግባር እንደገባንም ቃል በገባነው መሰረት በርካቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመኖሪያ ቤት የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በርካቶች የእድሉ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ የጥረታችን ውጤት አድማስ ሰፍቶም እንደ አገር የሪል ስቴት ዋጋው እንዲረጋጋ አድርገናል፡፡ ለግንባታው ዘርፍ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂም አስተዋውቀናል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ለአቅመ ደካማ ወገኖች በየጊዜው በተከታታይነት እንዲሁም በመደበኛነት በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ገንበተን መጠለያ ለወገኖቻችን በነጻ እያስረከብን ነው፡፡ ይኸውም ተግባራችንን አጠናክረን የምናስቀጥለውና ከምንም በላይ እጅጉን የምንኮራበት ነው፡፡
ኦቪድ የጀመረውን ሁሉም ዜጋ እንደየአቅሙ የቤት ባለቤት የማድረግ እና አቅመደካሞች ደግሞ በኦቪድ ፋውንዴሽን በኩል በነጻ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ የማድርግ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ጥላሸት የሚቀባ እና ሀሰተኛ መረጃ ተከታታይነት ባለው መልኩ በውጭ አገርና በአገር ውስጥ የሚገኙ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በኩል እየተስተዋሉ ነው፡፡ ከሐሰተኛ የሚዲያ ዘመቻ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ስሁት መረጃቸውን እዲያርሙ በተደጋጋሚ ጊዜ ማስጠንቀቂያና የእርማት መልዕክት እንዲደርሳቸው የማድረግ ሥራ ኦቪድ እየሰራ ቢቆይም በተለይ ‘‘መሰረት ሚዲያ እና ኢትዮ ፎረም’’ የሚባሉ ሃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች በዚሁ ተግባራቸው ቀጥለዋል፡፡
ደርጅታችን ኦቪድ እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገጾችና ግለሰቦች መቀመጫ አድራሻቸውን ሲያጣራ የቆየ ሲሆን በኦቪድ በውጭ አገራት የሚገኙ አጋር ደርጅቶች በኩል ጉዳዩ በሕግ እንዲታይ ለማድረግ የተከፈተውን የክስ ሒደት አጠንክሮ ይቀጥላል፡፡
ከዚህ በኋላም ማንኛውንም ዓይነት በድርጅታችን መልካም ስምና ዝና ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚቃጣ ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ ደርጅታችን እንደማይታገስና በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሰራም ያሳውቃል፡፡
ምንም እንኳ የዚህ ሐሰተኛ የመረጃ ስርጭት ምንጭና ዓለማ ምን እንደሆነ ክቡራን ደንበኞች በውል የሚረዱት ቢሆንም በነዚህ ሚዲያዎች የተሰራጨው የአሀዝ መረጃ ፣ የመረጃውን ሐሰተኛነት በቀላሉ ያሳያል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ አቤቱታ ቀረበበት በተባለው ሳይቶች የተጠቀሰው 700 የሚሆኑ ደንበኞች የቤት ገዥዎች የሌሉም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ አጠቃላይ ጉዳዩን በተመለከተ የሰጠነውን ዝርዝር ማብራሪያ በኦቪድ ሪል ስቴት በሁሉም የኦንላይን ሚዲዎቻችን በዝርዝር መመልከት ይቻላል፡፡
ኦቪድ የጀመረውን ሥኬታማ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ሥራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን አጠቃላይ ስለድርጅታችን ማንኛውንም ዓይነት መረጃ በአካልና በ9727 በመደወል ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን ልክቡራን ደንበኞቻችን እና ለማኅበረሰባችን በተከታታይነት መረጃ የምንሰጥም ይሆናል፡፡
መልካም የገና በዓል !
ኦቪድ ሬል ስቴት
ራዕያችን ልማት ነው!
2 comments
No
አትናገሩኝ ነው
የሚስራ ምንጊዜም ይተቻል
ይላል ተረቱ