ህገ ወጦችነም ለመቅጣት የተቀመጡት የቅጣት ህጎችም ተጋነዋል ተብሏል፡፡
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባዔው፤ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት አቅርቧል፡፡
ሪፖርቱን ያቀረበው ቋሚ ኮሚቴው ፤ የነዳጅ ግብይት ስርዓትን በተመለከተ በተዘጋጀው ረቂቅ ህጎች ላይ ህገወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ የሚደረጉ ቅጣቶችን አካቷል፡፡
ታዲያ የምክር ቤተ አባላት ሪፖርቱን ተንተርሰው ባነሱት ሃሳብ፤ የህግ ችግር የለብንም ችግሩ የሚወጡ ህጎች ስራ ላይ ይውላሉ ነው ወይ ብለዋል፡፡
ህጎች ሲወጡ ህዝቡን በስፋት ቢጠይቅም፤ መንግሰትን ግን ተጠያቂ ሲያደርጉ አይስተዋልም ሲሉ የምክር ቤት አባለቱ ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣናት የንግድ ቢሮዎች እንዲሁም የነዳጅ ባለስልጣናት እያወቁ ነው ነዳጅ የሚሸጠው ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት ሃሳበቸውን ግልጸዋል፡፤
ነዳጅ ዛሬ መጥቶ ነገ የለም ይባላል ይህ ደግሞ የመንግሰት ባለስልጣናት ትስስር በመኖሩ ነው ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
ታዲያ ከሚወጡ ህጎች ጋር ተያይዞ ሃሳባቸውን የሰጡት አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ህጎቹ መንግስትንም ይሁን የመንግሰት አካለትን ተጠያቂ ሊያደረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የሚወጡ ቅጣቶችን በተመለከተ ሃሳበቸወን የሰጡት አባላቱ በጣም ተጋኗል ያሉ ሲሆን ይህ ሊሻሻል ይገባል ብለዋል፡፡
ምክር ቤቱ መደበኛ ገባኤው እንደቀጠለ ሲሆን የነዳጅ ግብይት ስርዓትን በተመለከተ የተዘጋጀውነ ረቂቅ አዋጅ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Via: ኢትዮ ኤፍ ኤም