0
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በቻይና በሚገኙ ሆስፒታሎች ጭምብል ያጠለቁ በርካታ ሰዎች ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መሠራጨቱ ሌላ ወረርሽኝ ተከስቶ ይሆን የሚል ስጋትን አስከትሏል።
ከጉንፋን ጋር የሚመሳሰለው ‘ሂውማን ሜታኒሞቫይረስ’ (ኤችኤምፒቪ) በተለይም በልጆች ላይ በስፋት መከሰቱን ቤይጂንግ አምናለች። የተከሰተውም ከወቅቶች መቀያየር ጋር ተያይዞ መሆኑንም ገልጻለች።
ኤችኤምፒቪ እንደ ኮቪድ-19 አይደለም ሲሉ የሕብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች ገልጸዋል። ቫይረሱ ለአስርት ዓመታት የነበረ መሆኑን በመጥቀስ ቫይረሱ ሁሉንም ልጆች በሚባል ደረጃ በተወለዱ በአምስተኛ ዓመታቸው እንደሚያጠቃ ተናግረዋል።
ቫይረሱ በአንዳንድ ህጻናት ልጆች እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው በተዳከመ ሰዎች ላይ ከባድ ህመም ሊያስከትል ይችላል ሲል ቢቢሲ አስነበብቧል።
10 comments
Le Israel yargew😍
የመጨረሻው ዘመን ደርሷል ንሰሀ ግቡ 🙃
አንሰማም ከዚህ በፊት ኮሮና ብለው በውሸት የበዘበዙን ይበቃል
ጥምቀት ሲደርስ ነው እዴ …..💀
አይ ቻይና አሁንም ልትጫወትብን ይሆን?
shererit beltew new yeyazachew?
ቻይና አዲስ ቫይረስ አምራች ሀገር ይመችሽ👏
ምን ጉድ ነው ግን እነሱ ያገኝቱን ሁሉ እየበሉ እኛን ድጋሜ ልያስቀዝፉን ነው ደሞ😓😓😓
የሚበሉት ነገር ጉዳቱ እያመዘነባቸው ነው
አሪፍ ነዋ 👍