banner

በሰሜን ወሎ ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/2017 ዓ.ም በደረሰው “ምክንያቱ ባልታወቀ” የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ተገልጿል፡፡

የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉየ ረታ 4 ሺህ 560 ኩንታል የሚኾን 152 ክምር ላይ የደረሰው ቃጠሎ ጉዳት ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቁመዋል፡፡

የዋድላ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጽሕፈት ቤት ቡድን መሪ ምትኩ ሞላ በበኩላቸው እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ መኾናቸውን መግለጻቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡




10 comments

Berihu Gebremedhin Bright January 10, 2025 - 9:20 am

የእሳቱ መንስኤ ምንድነው?

Reply
Samri Kassa YNwa January 10, 2025 - 9:20 am

እግዛብሔር ሆይ ድረስልን ተጨንቀናል😭😭😭

Reply
Begashaw Nebiat January 10, 2025 - 9:21 am

So sad

Reply
Nuhamin Yitagesu January 10, 2025 - 9:21 am

በየሱስምምም

Reply
ዱብ እዳ January 10, 2025 - 9:22 am

😭😭😭😭

Reply
Oô Màryâm Lâmmà Sëbèktânï January 10, 2025 - 9:22 am

Los Angeles በረከቱ አደረብን ማለት ነው 😒

Reply
Dave Ababu January 10, 2025 - 9:22 am

ይህን ማን እንዳቃጠለው መገመት ኣያስቸግርምም በዚህም ይብቃን ማለት ነው ለፈጣሪ መንገርና መልሱ ከፈጣሪ ብቻ ነውው።

Reply
Ababo D Wahima AB January 10, 2025 - 9:25 am

ማራናታ አምላኬሆይ 🥹🥹

Reply
Kasahun Tamerat January 10, 2025 - 9:28 am

ቃድሞም አልተረሰም

Reply
Federalist Ethiopia January 10, 2025 - 9:28 am

“Mikiniyatu baltaweke”. Do’t try to hide their unacceptable behavior now.

Reply

Leave a Comment