የኢትዮጲያ ዲያስፖራ ማህበር በዚህ ዓመት ልዩ የሆነ የዲያስፖራ ንቅናቄን ለመፍጠር በማሰብ የኢትዮጲያ ዲያስፖራ ሳምንትን በአዲስ አበባ እና በቶሮንቶ ካናዳ እንደሚያካሂድ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።
ማህበሩ ከያዛቸዉ ዕቅዶች መሀከል አንዱ በሆነው በዚህ የዲያስፖራ ሳምንት! ዲያስፖራዉ የሚሳተፍበት፣ እርስ በእርሱ የሚገናኝበት፣ ቀደም ሲል በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተሰማሩ የዲያስፖራው አባላት ስለ ምርቶቻቸው የሚያስተዋውቁበት፣ የተለያዩ ተቋማትም ምርቶቻቸዉን እና አገልግሎታቸዉን ለዲያስፖራዉ የሚያሳዩበት እና የተለያዩ ይዘት ያላቸዉ ፕሮግራሞችን ያካተተ የመጀመሪያውን በዓይነቱ የተለየ የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ሳምንት ያዘጋጀ ሲሆን ቀጣይነት ያለው እና በየዓመቱ ሁሉን አሳታፊ በሆነ መልኩ እንዲቀጥል እቅድ ነድፎ እየሰራ እንደሆነ ተነግሯል።
በዚህ መረኃግብር የተለያዩ ዝግጅቶች ሲኖሩት የመጀመሪያው ዝግጅት ጥር 12 እና 15 በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል የተባለ ሲሆን ሁለተኛ የዳያስፖራ የእግር ጉዞ ከቦሌ ወደ መገናኛ ይደረጋል ተብሏል።በተጨማሪም የተለያዩ የፖናል ውይይቶች እንደሚኖሩት ተገልጿል።
የኢትዮጲያ ዲያስፖራ ማህበር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ዲያስፖራውን በማሰባሰብ ለሃገሩ የሚያደርገው አስተዋፅኦ ከማሳደግ ባሻገር ዲያስፖራውን እና መንግስትን በማቀራረብ እና ዲያስራው በሃገሩ ልማት ላይ ሲሳተፍ ለሚገጥሙት እክሎቸ ሁሉ መፍትሄ በማፈላለግ ሲሰራ ቆይቷል፡፡





1 comment
🖕