#FastMereja I ኤም ኤን ጂ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት እና ኩባንያ የፊልም ስክሪፕት ግዢ ስምምነት በዛሬው ዕለት በጌት ፋም ሆቴል በተካሄደ መረኃግብር ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ኩባንያው እየሰራ ከሚገኘው የፊልም ማርኬቲንግ ሥራ በተጨማሪ በፊልሙ ኢዱስትሪ ውስጥ ለመፍጠር ላልመው በጎ ተፅዕኖ የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገለፀ ሲሆን ኩባንያው በኢትዮጵያ ቢሮውን ከመክፈቱ አስቀድሞ ከፓራ ማውንት፣ ሶኒ ፒክቸርስ እና ሌሎች የፊልም ኩባንያዎች ጋር ሥራዎችን እየሰራ የቆየ ሲሆን በኢትዮጵያ ቢሮውን በከፈተ ማግስት በተለያዩ በጎ ተግባራትን ሲፈፅም እንደቆየም ሰምተናል።
በዛሬው ዕለት የተደረገው የፊርማ ሥነሥርዓት የፊልም ሀሳብ ያላቸው ደራሲያን ስክሪፕታቸውን ሸጠው በሌሎች አካላት ሥም ለዕይታ ይበቃ የነበረበትን ልማድ በማስቀረት ደራሲያን በፊልም ፕሮዳክሽን ውስጥ እውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ለማሳየት የተደረገ እንደሆነም ከመድረኩ ለማወቅ ችለናል።
የኩባኛውን በኢትዮጵያ ሥራ መጀመር በማስመልከት በመጀመሪያ ለወደቁትን አንሱ የነድያን መርጃ ማሕበር የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከ6 ወር በኋላ ደግሞ ለንሕምያ የኦቲዝም ሴንተር የተለያዩ የንፅሕና እና መማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግ ችሏል።




