banner

ዶ/ር አያኖ በራሶ ተሸለሙ!

ትናንት በሮሪ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደው የሽልማት ስነ_ስርዓት ላይ የተገኙት የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ም/ቤት አፈ -ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እንደተናገሩት ሽልማቱን ያበረከቱት የዩኒቨርስቲው እና የሀሃዋሳ ከተማ ማህበረሰብ አባላት ናቸው ብለዋል

አፈ-ጉባኤዋ እንዳሉት በእርግጥም ዶክተር አያኖ በአመራርነት በቆዪባቸው ጊዜያት ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና ዩኒቨርስቲ መልካም ስራ ሰርተዋል ።

በሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ሲጀመር ከዲስ መንገድ ማውጣትና ግንባታዎችን ማፍረስ ያላስፈለገው ቀደም ሲል ዶክተር አያኖ በሀዋሳ ማስተር ፕላንን ለነዋሪዎች ምቹ አድርገው በመስራታቸው መሆነነው ።

ወ/ሮ ፋንታዬ እንዳሉት ዶክተር አያኖ ህዝብን በታማኝነት በማገልገል መልካም ስራ መስራታቸውን በማሰብ ይህን ስጦታና ምስጋና ያበረከተው ማህበረሰብም በእጅጉ ሊመሰገን ይገባል ።በማድረጉ በእጅጉ ሊመሰገን ይገባል ።

ሽልማቱ የተበረከተላቸው ቀደም ሲል የከተማው አስተዳደር ከንቲባ እና የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት በነበሩበት ጊዜ ላበረከቱት ጉልህ አሰተዋፅኦና ላስመዘገቡት ውጤት ነው ።

ሽልማቱን ያበረከቱት የዩኒቨርስቲው እና የሀሃዋሳ ከተማ ማህበረሰብ አባላት አንደሚሉት ዶክተር አያኖ ቀደም ሲል የከተማው አስተዳደር ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ ከተማዋ ፅዱ፣ውብና ለመኖሪያ ምቹ እንድትሆን ጉልህ ተግባራትን አከናውነዋል ።

ከተማዋ አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ እንድትደርስ ፣ በተለይም የመኖሪያ መንደሮቿ አረንጓዴ መናፈሻዎች እንዲኖራቸው እንዲሁም አንድ ዘመናዊ ከተማ ሊያሟላ የሚገባው ማስተር ፕላን እንዲኖራት ዶክተር አያኖ መሠረት የጣሉ አመራር መሆናቸውንም ይገልፃሉ ።

ዶክተር አያኖ በከንቲባነት ቆይታቸው ግራ ቀኝ የእግረኛ መንገድና የጎረፍ መውረጃ ቦይ ያለው ከ25 ኪ/ሜትር በላይ የአስፋልት መንገድ በማሰራት የትራፊክ እንቅስቃሴውን እንዲሳለጥ አድርገዋል እንዲሁም ተማዋን ከጎርፍ አደጋ ታድገዋል ።

ከተማዋን ፅዱና አረንጓዴ እንድትሆን ካከናወኑት ስራቸው በተጨማሪ ዶክተር አያኖ በከተማዋ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮብል ስቶን ንጣፍ በማስጀመር ለመኖሪያ ምቹ እንድትሆን ጉልህ የአመራርነት ሚና የተወጡ የመጀመሪያው ከንቲባ ናቸው።

ዶክተር አያኖ በራሶ የዩነሸርስቲውን ግንባታ ማስፋፋት ጨምሮ ግቢውን በማስዋብ እንዲሁም በትምህርት አፈጻጸም ረገድ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በማውጫ ፈተና ውጤት ተቋሙ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን የተጉ ናቸው ።

ይኸውም ፣ከሚመለከተው የመንግስት አካላት ጋር በመወያየትና በጀት በማፈላለግ ለሌሎች አጎራባች ክልሎችም ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ በ17 ሚሊዮን ዶላር በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የኦክስጂን ፕላንት ማቋቋም መቻላቸው ፣ ዩኒቨርስቲው ከነበሩት 4 ካምፓሶች ወደ 7 እንዲያድግና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ማስቻላቸው ለአብነት የሚጠቀስ ነው ።

እንዲሁም መንግስታዊ ላልሆኑ ሀገር በቀል ድርጅቶች የነበራቸው ተባባሪነትም ተጠቅሷል።
በተለይም ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ በቀናነትና በውሳኔ ሰጭነት ለማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በማሳያነት ቀርቧል። በዚህም በሜሪጆይ ሀዋሳ የወጣቶች ማዕከልና አረጋዊያን ማዕከል ያሳረፉት አሻራ የሚዘነጋ አይደለም። ለዚህም ማረጋገጫ ከሁለት አመት በፊት የሜሪጆይ ወጣቶች ማዕከል የቤተ- መጽሀፍት በስማቸው መሰየሙ አበርክቶአቸውና የነበራቸውን ጉልህ አሻራ ማሳያ እንደሆነም ተገልጿል።

በዚህ የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደን ጨምሮ ዶ.ር ፍሰሃ ጌታቸው የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም. ፕሬዝዳንት፣ ፓስተር ዮሴፍ ዮና ሀዋሳ ከተማ አብያተ ክርስትያናት ህብረት ካውንስል ፕሬዝዳንት እና ሌሎች አመራሮች ፣የተለያዩ ባለሀብቶች የዩኒቨርስቲው ማናጅመንት አባላት ፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት መሪዎችና የተሸላሚው አድናቂዎች ተገኝተዋል ።





3 comments

Minab Girma January 13, 2025 - 10:05 am

“ታጠበ” ማለት ይሄ አይደል?

Reply
Tesfaye Tagele January 13, 2025 - 10:12 am

ይገበዋል።

Reply
Yohanan Yokamo January 13, 2025 - 10:15 am

#ዶ/ር አያኖ – ይገባዎታል!
#ክብር ለሚገባው ሰው የሚገባውን ክብር መስጠት የአክብሮት ግዴታችን ነው። ከህብረተሰቡ ከወዳጆቹ በአይነቱ ለየት ያለ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። ለሀገር ለወገን የደከመን ሰው ማሰብና መሸለም ባህላችን ይሁን።
#እግዚአብሔር እድሜና ጤና ያብዛሎት ዶ/ር።

Reply

Leave a Comment