banner

በርካታ ሰዎች በአደንዛዥ እፅ ዝውውር ላይ በሆንግ ኮንግ ለእስር እየተዳረጉ ነው ተባለ።

#FastMereja I ቮይስ ፎር ፕሪዝነርስ (voice for prisoners) መስራች የሆኑት ጆን ዎተርስፑን እና ጄን ቾው የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን በመቀነስ ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ እንዲኖር እየሰሩ እንደሆነ ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።

በአሁኑ ጊዜ ግንዛቤ ለመፍጠር በአፍሪካ የሦስት ሳምንት ጉዞ እያደረጉ ሲሆን ከኢትዮጵያ በፊት በኬንያ እና በኡጋንዳ ውጤታማ ጉዞ ማድረጋቸውን ተናግሯል። በጉዟቸው ወቅት ከቀድሞ እስረኞች፣ አሁን በሆንግ ኮንግ ከሚገኙ እስረኞች ቤተሰቦች፣ ጋዜጠኞች እና ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን አስመልክተው ግንዛቤ መስጠታቸውን ገልጻል።

የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንደ ሲንጋፖር፣ ቻይና፣ ኢንዶኔዥያ፣ ታይላንድ እና ፊሊፒንስ ባሉ አገሮች የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ረጅም አመት እስራት አልፎ ተርፎም የሞት ቅጣት እንደሚያስከትል አስጠንቅቋል።

“Voice for Prisoners” በ2018 በሆንግ ኮንግ የተመሰረተ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በፀረ-አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ላይ እና እስረኞች በእስር ከቆዩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መፈታት እና አንዳንዴም ከተለቀቁ በኋላ ድጋፍ እና ተስፋ ለመስጠት አላማ አድርጎ የሚሰጥ ድርጅት ነው።




Leave a Comment