banner

ሳምንታዊ የስራ ቀናትን ወደ አራት ቀናት የማውረዱ እቅድ በብዙ ሀገራት ተቀባይነት እያገኘ ነው ተባለ

ከአራት ዓመት በፊት የኮሮና ቫይረስ ሲከሰት የተለመዱ የስራ ባህሎች እንዲቀየሩ አስገድዶ ነበር፡፡ ለአብነትም ከቤት ሆኖ መስራት፣ ለሰራተኞች በቂ እረፍት መስጠት፣ የስራ ሰዓትን መቀነስ እና ሌሎችም እርምጃዎች ተወስደው ነበር፡፡

የቫይረሱ ስርጭት ከቀነሰ እና ህይወት ወደ ቀድሞ መመለስ ሲጀምር ግን ከቤት ሆኖ መስራት እና ሌሎች አሰራሮች በዛው ቀጥለዋል፡፡

ሳምንታዊ አራት የስራ ቀናት ማለት ሰራተኞች ሳምንታዊ ስራቸውን ሙሉ ለሙሉ በተጠቀሱት ቀናት መስራት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ደመወዛቸው ደግሞ አምስት ቀናት እንደሰሩ ተደርጎ ይከፈላቸዋል የሚል ነው፡፡

በተለይም ሰራተኞች የተሻለ እረፍት ሲያገኙ ተጨማሪ ስራዎችን የመስራት ፍላጎታቸው መጨመር፣ የተቋማት አትራፊነት መጨመር እና ሌሎችም ጥቅሞች እየታዩበት መምጣታቸው ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ቤልጂየም የሰራተኞችን ምርታማነት እና የተቋማትን ውጤታማነት ለማሳደግ በሚል አራት የስራ ቀናትን ለሙከራ በተወሰኑ ተቋማት ላይ ከተገበረች በኋላ ውጤታማ ሆኖ በመገኘቱ በይፋ ሳምንታዊ የስራ ቀናትን ከአምስት ቀናት ወደ አራት ቀናት ዝቅ አድርጋለች፡፡

ሰራተኞች በሳምንት አራት ቀናት መስራት ከጀመሩ በኋላ የአዕምሮ ጤናቸው ለውጥ ማሳየቱ፣ ጫናዎችን በመፍራት ቤት ውስጥ ይውሉ የነበሩ ዜጎች የመስራት ፍላጎት ማሳየታቸው፣ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሉን እና ሌሎችም ለውጦች እንደመጡ የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ደ ክሮ ተናግረዋል፡፡

ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ ከቤልጂየም በኋላ ብሪታንያ የአራት ስራ ቀናትን በ61 ኩባንያዎች ላይ ለስድስት ወራት ከሞከረች በኋላ ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ ይፋዊ የስራ ቀናትን ወደ አራት ቀናት ዝቅ ለማድረግ በሂደት ላይ ነች ተብሏል፡፡

የአውሮፓ ባለግዙፍ ኢኮኖሚዋ ጀርመንም ይህን የአራት ስራ ቀናት እቅድን በሙከራ ደረጃ በመተግበር ላይ እንደሆነች ተገልጿል፡፡

ከጀርመን በተጨማሪ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣ ስዊድን ፊንላንድ እና ሌሎችም ሀገራት የሰራተኞቻቸውን የስራ ቀናት ወደ አራት ቀናት ዝቅ ለማድረግ በሂደት ላይ እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ዘገባው የዐል ዐይን ነው።

10 comments

Oniv Brezzy January 15, 2025 - 7:38 pm

1 ብቻ ቢሆን ደሞ ይመረጣል 👍

Reply
አማኑኤል አበራ January 15, 2025 - 7:40 pm

የቀረው በሙሉ በዲይቲ ስሆን ደግሞ አንደኛ ነው😂😂

Reply
Sham Kind January 15, 2025 - 7:41 pm

በተለይ ብልፅግና ቢሮ የምትሰሩ ሰዎች ጭራሽ ባትሄዱ ባይ ነኝ 😔

Reply
Mundino Alemu Mohammed January 15, 2025 - 7:42 pm

እኛ ጋ በማክሮ ኢኮኖሚን ምክንያት በማድረግ ከ5 ወደ 6 ከፍ አድርገነዋል ለዛውም 7/24ትን ጨምሮ 😁

Reply
Kumera G Akuma January 15, 2025 - 7:43 pm

እ/ያ ውስጥ እኮ ለ ሰራተኛው ከምከፈለው አንፃር በሳምንት ሁለት ቀን መስራት ራሱ ቡዙ ነው 😏

Reply
Kidanu Alemayehu January 15, 2025 - 7:45 pm

እኛ ሀገር በአግባቡ ሁለት ቀን የሚሰራ የለም

Reply
Mekonnen Fuche January 15, 2025 - 7:48 pm

ጁማዓ Mubarak አርብ ናት!?

Reply
Getafea Arega January 15, 2025 - 7:48 pm

ፋስቶች ይህ ወንድማችን Yonas Mesfen ይባላል በኩላሊት ህመም እየተሰቃየ ነው እባካችሁ ለነ እዚህ ልጆቹ ብላቹ ፖስት አድርጉለት ሙሉ መርጃ ከራሱ ትገኛላችሁ የእጅ ስልክ 0917312993

Reply
Belief Love Hope January 15, 2025 - 7:52 pm

የኛ አገር ግን ወደ 6 ቀን ከፍ ለማድረግ ነው ዕቅዱ kkkk

Reply
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ January 15, 2025 - 7:57 pm

ቀበሌያችን ግን ከሁሉ ቀድሞ በሳምንት 2ቀን ብቻ ነው የሚሰራው 😂

Reply

Leave a Comment