ሀገርን ያኮሩ ጀግና ተጫዋቾችን ያሳየን….ለበርካታ የክልል ክለቦች ምስረታም ሆነ የዋንጫ ስኬት ቀዳሚ ምሳሌ የሆነም ክለብ ነው። (ሀዋሳ ከነማ)
ላለፉት ተከታታይ አመታት ግን ስኬቱ ብቻ ሳይሆን የቀደመ ማንነቱ ….በታዳጊዎች አቅም የምንገረምበት መገለጫውም ጭምር ከሙሉ ውጤታማነቱ ጋር ጠፍቷል!!!
በታሪክ ከሊጉ ወርዶ የማያውቀው ይህ አንጋፋ እና ታሪካዊ ቡድን አሁናዊ መልኩ ያስፈራል…አሁን መንቃት ኃላ ከመቆጨት ያድናል!!!
የሀዋሳ ከነማ ጉዳይ ….
አይደለም ቡድኑን እያየ ላደገ የከተማው ተወላጅ ቀርቶ እግርኳስን ለሚል የሀገራችን ስፖርት ቤተሰብ የሀዋሳ ከነማ ጉዳይ ይመለከተዋል፡፡ አሁን ላይ የቡድኑ ችግር አፍጥጦ መጣ እንጂ ከጀመረው ሰነባብቷል እኮ …
በእኔ ምልከታ የቡድኑ ችግር ከፊት የሚታዩ ሰዎች ብቻ አይደሉም(እነሱ ሁኔታውን ያባብሳሉ ይሆን እንጂ) መሰረታዊ ችግሮች ሌላ ናቸው፡፡
መሰረታዊ ችግርች ምንድን ናቸው ታዲያ ?
1ኛ, የመዋቅራዊ/አደረጃጀት ችግር
ሀዋሳ ከነማ ከመንግስት አስተዳደር መዋቅር ወጥቶ በህዝባዊ የእግርኳስ ቡድን ሀሳብ በቢዝነስ ተቋም የልቦናውቅር(Mindset) ራሱን ማስተዳደር እስካልጀመረና ከተማ አስተዳደሩ የቡድኑ ዋነኛ ባለድርሻ እንጂ ፈላጭ ቆራጭ ባለቤት መሆኑን እስካልተወ ድረስ ችግሩ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
**
2ተኛ, ከሜዳ ውጪ ያለ አስተዳደራዊ ችግር
እንደ እግርኳስ ቡድን ያውም በሀገሪቱ የማይሻር ታሪክ እንዳስመዘገበ ቀደምት ቡድን እንዲያስተዳድሩ የሚመረጡ ግለሰቦች ከእግርኳሱ ዘርፍ ጋር ቁርኝት ያላቸው እስካልሆኑና ሲያጠፉ የሚኮንን ሲያለሙ የሚያበረታ በተሰራው ልክ ተጠያቂነት የሚያሰፍን አስተዳደራዊ ስርዓት እስካልተበጀ ድረስ ችግሩ ይቀጥላል፡፡
***
3ተኛ, የስትራቴጂካዊ እቅድ ችግር
የቡድኑን ታሪካዊ ዳራ በሚመጥን ደረጃ እግርኳሳዊ ስትራቴጂ፣ የሚታይ, ታማኝነት ያለው፣በጊዜ የተገደበ የሥኬት እቅድ፣ የቡድን አወቃቀር በወጣቶችና ታዳጊዎች ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገመግምበት፣ የፋይናንስ አቅሙን የሚያጎለብትበት ከወጪ ማዕከልነት ወጥቶ በራሱ ገቢ የሚያመነጭበት አሰራር፣ በአጠቃላይ ቀጣይ መዳረሻውን የሚያሳይበት ስትራቴጂክ እቅድ በይፋ እስከሌለውና ልጓም እስካልተበጀለት ድረስ የቡድኑ የስኬትም ሆነ የውድቀት ጉዞ በነሲብ ነው የሚቀጥለው፡፡
****
4ተኛ, ቡድኑ የሜዳ ውስጥ እግርኳሳዊ ሁኔታን የሚገመግምበት ስርዓት
የቡድኑ አጠቃላይ የጨዋታ ዘይቤ፣የአሰልጣኞችና የተጨዋቾች ምልመላ ስርዐት፣ የተጨዋቾች ብቃት መመዘኛና የክፍያ ምጣኔ ስርዓት፣ በአጠቃላይ ለቴክኒካዊ ጉዳዮች የሚሰጠው ትኩረት እግርኳሳዊ እስካልሆነ ድረስ በግለሰቦች (ተጨዋቾች፣አሰልጣኞች እንዲሁም ሌሎች አባላት) ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ጉዞ ይሆናል፡፡
#ሲጠቃለል
ሀዋሳ ከነማ ከጥገኝነት ተላቆ፣በእግርኳስ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን ተምሳሌታዊነቱ እንዲቀጥል፣ በቡድኑ መኖር ጥቂት ግለሰቦች የሚጠቀሙበት ብቻ ሳይሆን ህዝባዊ ሆኖ እንዲዘልቅ፣በየዓመቱ ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ብቻ ሳይሆን ከራሱ አልፎ ለሌሎች የእግርኳስ ልማቶች ገቢ የሚያስገኝ ትሩፋት እንዲኖረው፣ የቡድኑ ዋነኛ ባለቤት ደጋፊዎችና ባለድርሻዎች እንጂ ተዋንያኖች( አሰልጣኝም ሆነ ተጨዋች ጥቅም እስካገኘ ድረስ ወደፈለገው ቡድን እንደሚሄድ ታሳቢ በማድረግ) አለመሆናቸውን አረጋግጦ ለቡድኑ ባለቤቶች ትኩረት የሚሰጥ አሰራር እንዲመጣ ጥገናዊ ለውጥ(Reform) ሳይሆን ስርነቀል የአደረጃጀትና የመዋቅር ለውጥ በእጅጉ ይፈልጋል፡፡
ይህ እስካልሆነ ድረስ ሰዎች ቢሄዱ ሌሎች ሰዎች ይመጣሉ ያው ”በአሮጌ አቁማዳ አዲስ ወይን መቅዳት ነው..” የሚሆነው ለዚህ ነው ጉዳዩ የሰዎች ብቻ አይደለም ያልኩት ይሁንና ሰዎች ለስኬትም ለውድቀትም የሚኖራቸው ሚና ከፍ ያለ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡
#መውጫ
ታሪክን የኃሊት …
ሀዋሳ ከነማ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ጨዋታ በአሸናፊነት ያጠናቀቀው ከዛሬ 27 ዓመት በፊት መብራት ሃይልን 3 ለ 2 አሸንፎ ነበር፡፡
ወርሀ ህዳር 1990 ዓ.ም
ሀዋሳ ከነማ እንዳድን ሪፎረም ያስፈልገዋል… የህዝብን ሃብት፤ የህዝብን ንብረት ብሎም የህዝብን ታሪክ በትኩረት እንመልከት።
ፀጋአብ ዳዊት


5 comments
Tsegaab 👏
Marko Z Beloved MT
Miskir የማን ነው ይሄ ነገር 🤔
ሲጀመር እግርኳሳችን ከመንግስት እጅ ወቶ ክለቦች እራሳቸውን ካልቻሉ መቼም አያድግም
Hawassa kenema😭😭😭