banner

የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን እንድትስት ካደረገ በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ በመጨመር የቆረጠውን እግሯ ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኋላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ539/1/ሀ/ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

10 comments

Lij Muba January 24, 2025 - 7:42 am

መንግስት የከተፈዉሳ😉

Reply
Ethiopia Yehulachin Nat January 24, 2025 - 7:44 am

አረሰውን እንኳን ባትፈሩ ፈጣሪን ፍሩ ተቀባብላቹ እንዲ አይነት አፅያፊ ዘገባ አትዘግቡ በጣምም ፀያፍ ዘጋባ

Reply
Only Mother Lover January 24, 2025 - 7:46 am

ሰምተናል 👹💀 በቃ ????!

Reply
Biruk Gusa Biruke Gusa January 24, 2025 - 7:46 am

Etihiopa wust ihe gn begeta😭😭😭

Reply
እዮብ መኮንን January 24, 2025 - 7:46 am

ፋስት ግን መቼ ነው ጥሩ መረጃ የምትነግረን ?

Reply
He Nok January 24, 2025 - 7:48 am

dnkem kidus ፐ

Reply
Selehadin Al Ayubi January 24, 2025 - 7:48 am

አላህ ይዘንልን እንጂ ይሄ ድርጊት እንኳን ለማድረግ ለማንበብም ይከብዳል

Reply
Sami Sam Tesfu January 24, 2025 - 7:49 am

ችግሩ ውሳኔው ሚተገብረው የለም እንጅ 😢😢😢

Reply
As Ne January 24, 2025 - 7:50 am

በስመ አብ ወወልድ አቤቱ ማረን

Reply
حسان عبد بأر January 24, 2025 - 7:51 am

ጠብሶ በላ አለማለታቹም!

Reply

Leave a Comment