0
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተርናሽናል ሆቴል 300 ሺህ ብር መቀጣቱን እና ቦታውን እንዲያጸዳ መደረጉን የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በከተማዋ ውስጥ የተለያዩ ስራ ላይ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶች እና ግንባታ ገንቢዎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
10 comments
ኣሩ በል እንጂ ምን አሰፈራህ
የአንድ ጊዜ ነው ወይስ በተደጋጋሚ 😀
አይምሮውዐቸውንም እንዲያፀዱ ቢደረግ
በየመንደሩ ዝናብን ተገን በማድረግ የሚለቁ መኖሪያ ቤቶች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰድባቸው።
ኸረ ድፍረት 😂የሰገራው ፍሳሽ ዘንባባ ነክቷል ወይስ አልነካም ዋናው ጉዳይ እሱ ነው 🤔
ጥሩ ስራ ነው
አንድ ሰው በመኪና ሲገጭ 80ሺ ነው 🤣
ኮሪደር አስፋልት ምንድነው? አስፋልት ካልክ አይበቃም? ሆቴሉ ትልቅ ስህተት ሰርቷል ግን ቅጣቱ በጣም በዛ
ጨለማን ተገን ማድረጉ በምን ተረጋገጠ 🤣🤣😁😁
ኮሪደር ልማት ጋርም ጨለማ አለ እንዴ??