የኦሮሚያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ መግለጫ እንደሚያሳየዉ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ በምስራቅ ባሌ ዞን ዳዌ ካቼን ወረዳ ኦዳ በተባለ ቀበሌ ዉስጥ ነዉ ። ተከሳሽ ኢብሲቱ አህመድ አሊዬ የተባለችዉ ግለሰብ የ4 እና 5 አመት እድሜ ያላቸዉን ሁለት ህፃናት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ገላችሁን ልጠባችሁ በማለት ወደ ዋቤ ወንዝ በመዉሰድ ከገደለቻቸዉ በኋላ ወንዝ ዉስጥ እንደጨመረቻቸዉ መግለጫዉ አመላክቷል ።
የልጆቹ ቤተሰቦች ህፃናቱ በመቆየታቸዉ ባደረባቸዉ ስጋት ከአከባቢዉ ሰዎች ጋር ፍለጋ በማድረግ በነጋታዉ የሁለቱም ህፃናት አስክሬን ወንዝ ላይ ተንሳፎ መገኘቱ ተረጋግጧል ። ፖሊስም የሁለቱን ህፃናት አስክሬን ከወንዝ ዉስጥ በማዉጣት የአስክሬን ምርመራ በማድረግ ተከሳሻ ላይ ክትትል ማድረጉ ተገልጿል ። ከ4 ቀናት ክትትል በኋላ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከተሸሸገችበት በቁጥጥር ስር ዉላለች ። በቁጥጥር ስር ከዋለችም በኋላ በሰጠችዉ ቃል ልጅ መዉለድ ባለመቻላ ባለቤቷ ፊት እንደነሳትና ወደ ሌላኛዋ ሚስቱ እና የልጆቹ እናት ፊቱን በማዞሩ በቅናት በመነሳሳት ድርጊቱን መፈፀሟን ተናግራለች ።
ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በበቂ ማስረጃ አጠናቅሮ ለአቃቤ ህግ ልኳል ። አቃቤ ህግም የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ በከባድ የግድያ ወንጀል ህግ 539 ንዑስ አንቀጽ 1መሠረት ክስ መስርቶበታል ።የተመሠረተዉን ክስ ሲከታተል የቆየዉ የምስራቅ ባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሻ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፋን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከኦሮሚያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ያገኘዉ መረጃ ያሳያል።
7 comments
መልከም ዜና ናፈቀን ኡፍ😭😭😭
አልተገነዘብነዉም እንጅ የመጨረሻዉ ዘመን ደርሠናልኮ
አቃፊ ና የጉዲፈቻ መስራች ነን ብለውን?
እባካችሁ የባሰ ግፍ ግፍ ለኛ አትንገሩን🥺🥺🥺
Inalillay…
እግዞ…እግዞ…
በኢየሱስ ስም
Lezich midir firid yinesat?😭😭😭😭😭😭😭😭