banner

ሕንጻ የሚበቅልባት ከተማ!

ከሚዛን ከወጣሁ አራት ዓመት ከምናምን ሆኖኛል፤ በመሀል አልተመለስኩም። ከፍተኛ የመምጣት ጉጉት ቢኖረኝም ሊሳካልኝ አልቻለም። ነገሮች ሰመሩና ዛሬ ሚዛን እገኛለሁ። እንዴት ደስ እንዳለኝ።

ሚዛን እንደተለመደው ማልዳ ነው የምትነቃው፤ የሰው ብዛት የቢዝነስ እንቅስቃሴው መነቃቃት ከማውቀው በላይ ብሶበታል (በነገራችን ላይ ሚዛን ሌሊትም ንቁ ናት)።

ከማዘጋጃ እሰከ ከዋና አደባባይና ማርያም ድረስ ከጴጥሮስ ወንዝ እስከ ቤንች ፍሬ ከማደያ ጀርባ እስከ ስቴዲየም ከከፋ በር እስከ ዋና አዳራሽ እንዲሁም ከመናኸሪያ እስከ ቦርሳ በሁሉም አቅጣጫዎች ዞረናል።

የምር ለከተማዋ እንግዳ እስክመስል ድረስ ግራ ተጋብቻለሁ። እዚህም እዛም አዳዲስ ሕንጻዎች እየተገነቡ ነው። ብዙዎቹ አልቀዋል ስራም ጀምረዋል፤ ብዙዎቹ በሂደት ላይ ናቸው ለማጠናቀቅ ጥድፊያ ላይ ናቸው። በጣም ብዙዎቹ ደግሞ ጅምር ላይ ናቸው። ከዚህም በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታጥረው የግንባታ ግብአት እያቀራረቡ ነው። በቃ ይህ ነው እየሆነ ያለው። ብቻ የሚታየው ሁሉ አዲስ ከተማ እየተገነባ ነው የሚመስለው። ሕንጻ ይበቅልባታል ቢባል ግነት አይደለም።

ሁሉም ሲጠናቀቁ ስራም ሲጀምሩ የሚፈጠረውን ድባብና ውበት ሳልኩት። ብዙ ከተሞች የንግድና የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸው በተቀዛቀዘበት በአሁኑ ወቅት ሚዛን የበለጠ ጎምርታለች።

እዚህ ላይ ያደርኩበት ሳላይሽ ዘግራንድ ራሱን ችሎ ብዙ የሚወራለት ስለሆነ ነው ያልጠቀስኩት።

ጋዜጠኛ ጥላሁን EBS ቴሌቪዥን





Leave a Comment