0
#FastMereja I የወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ ተከትሎ ደግሞ
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቐለ ዲስትሪክት ሰራተኞች እንደሰማነው በማለት ዶቼ ቬለ እንደዘገበው ከወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ በኃላ በነበሩ ሶስት ቀናት ብቻ ከግማሽ ቢልዮን በላይ ብር ከባንኩ ቅርንጫፎች በደንበኞች ወጪ ተደርጓል።
በገበያዎች በተለይም የምግብ ነክ ሸቀጦች የሚገዛ በዝቷል፥ የተወሰነ የዋጋ ጭማሪም ይስተዋላል። በሌላ በኩል በበርካታ ነዳጅ ማደያዎች በተለይም ቤንዚን የሌለ ሲሆን በጥቁር ገበያ ከ270 እስከ 300 ብር አካባቢ ይሸጣል። ይህንኑ ተከትሎ የትራንስፖርት ዋጋም ተወዷል ሲል ዶቼ ቬለ አስነብቧል።
10 comments
ከዚህ በኋላ የምታድኑት ከተማ የለም፣ እጅ ስጡ
ህዝቡ ከፈራ ደብረ ፂዮን እና ጌታቸው ረዳ ለምን በግል አይጣሉም😏
አቦ የምወደውን ህዝቡ አታሰቃዩብኝ😡🥺
ምን አይነት አርመኒ ስልጣን ፈላጊዎች ናቸው ዘላለም ጦርነት እጭ በሰው ድም መጫወት
ፈጣሪ ሆይ ሰላም ለሰሜን ኢትዮጵያ 🤲
ጌታቸዉ ረዳ ሲፋቅ ብልጽግ ነዉ ፡፡
ጦርነት ስወዱ💔
ምን አለበት ህዝቡን እረፍት ብሰጡት?
ልክ ናቸው ሰው አንዴ ነው እሚሸወደው
ያሳዝናል የመቀሌ ሕዝብ ስቃይ!
እባካችሁ ጌታቸው እና ደብረጽዮን ከህዝብ ላይ ውረዱና የግል ጉዳያችሁን በግል ጨርሱ!
ህወሃት እና ብልፅግና ያለ ጦርነት ጨጓራቸው አይፈጭም