banner

ስለ እናትዎ ፅፈው ይሸለሙ

አምስት ቀናት ብቻ ቀርተዋል !!!
****
እናት ባንክ ለኢትዮጵያ እናቶች መታሰቢያ ይሆኑ ዘንድ ያዘጋጃቸው ሽልማት የሚያስገኙ ሁለት እናት ተኮር የስነ ፅሁፍ ውድድሮች ላይ በርካቶች ስለ እናቶቻቸው እየፃፉ እየተወዳደሩበት ይገኛሉ።

የዚህ ውድድር የፅሁፍ ማስገቢያ ቀን ሊጠናቀቅም አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ውድድሩ ለእርሶም ክፍት ነው፤ በቀሩት ቀናት ከአሁን ጀምሮ ስለ እናትዎ ፅፈው ይወዳደሩ፣ ያሸንፉ፣ ይሸለሙ።

* የውድድር አይነቶች

1- “የዓመቱ የእናት ባንክ ድንቅ እናት” –
ተወዳዳሪዎች በአካባቢያቸው የሚያውቋቸውን ወይም የራሳቸውን እናቶች፣ በድምጽና በምስል ቀርጸው በቀጥታ በመጠቆም የሚሳተፉበትና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ ውድድር።

2- “ለእናቴ” –
በዋናነት ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ (ግጥም ያልሆነ፣ በወግ መልክ፣ በደብዳቤ ቅርፅ ወዘተ.) የሚገልፅበትና “ለእናቴ” የሚልበት መልካም አጋጣሚ ነው።

* የዓመቱን ድንቅ እናት ውድድር

ይሄ ውድድር በሕይወት ያሉ እናቶች የሚመሰገኑበት የውድድር አይነት ሲሆን ከ “ለእናቴ የፅሁፍ ውድድር” የሚለይባቸው የራሱ መመዘኛዎች አሉት፤ መወዳደሪያ መስፈርቶቹም፡-

➢ ለውድድር የሚቀርቡት ባለታሪኮች በሕይወት ያሉ እናቶች መሆን አለባቸው፤
➢ ታሪካቸው የሚነገርላቸው እናቶች ግዴታ ወላጅ እናት (የስጋ እናት) መሆን አይጠበቅባቸውም፤ ለምሳሌ አሳዳጊ ወይም ደግሞ በሰፈር አሊያም በጎረቤት ያሉ እናቶችን ታሪክ ማቅረብ ይቻላል።
➢ በዚህ ውድድር ላይ ስለ ሚያቀርቡት ታሪክ ከፈለጉ በጽሑፍ አሊያም በድምፅ ወይንም ደግሞ በቪዲዮ ሥራዎቻቸውን ቀርፀው ማቅረብ ይችላሉ።

➢ ውድድሩ የሚቆይበት እስከ ጥር 30/17 ዓ.ም.. ይሆናል።

➢ መወዳደሪያ ሥራዎቻችሁን አቅራቢያቸሁ በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች ማስረከብ የሚቻል ሲሆን በቪዲዮና በድምፅ ቅጂ ለምታስገቡ እና ውጭ ሀገር ለምትኖሩ ደግሞ በኢሜል፤ አሊያም በእናት ባንክ ኦፊሻል የፌስቡክ ገፃችን ላይ መልዕክት ማስቀመጥ ይችላሉ።

ለእናቴ የጽሑፍ ውድድር የውድድር ጽሑፎቹ መወዳደሪያ መስፈርቶች፡-

➢ በሌሎች የኅትመት እና የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ያልቀረበ ወጥ፣ አዲስና የተለየ መሆን ይኖርበታል፤

➢ ጽሑፉ ግልጽ እና ተነባቢ እንዲሆን በኮምፒውተር ተጽፎ፣ በ12 ፎንት የፊደላት መጠን እና በ1.5 የኅዳግ መስመር መቅረብ አለበት፤

➢ በ ኤ ፎር (A4) የወረቀት ምጣኔ፣ ከሦስት /3/ ገጽ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል፤

➢ ለተመረጡ አሸናፊ ጽሑፎች የገንዘብ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ይበረከትላቸዋል፤

➢ ተወዳዳሪዎች፣ ስማቸውን እና አድራሻቸውን የጽሐፍ ሥራቸውን ባቀረቡበት ወረቀት ላይ መጻፍ የለባቸውም፤ ይልቁንም _ ሥራቸውን በሚያሽጉበት ፖስታ ላይ ብቻ መጻፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

➢ እናት ባንክ አሸናፊ ጽሐፎችን በተለያዩ መንገዶች ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡

➢ የማስረከቢያ ጊዜ ጥር 30/2017 ዓ.ም. ፡፡

➢ ተወዳዳሪዎች ጽሑፋቸውን በአቅራቢያቸው በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የውድድሩ መዝጊያ በተመለከተ የተወሰኑ የውድድሩ ተሳታፊዎች፣ የውድድሩ አሸናፊዎች፣ ጥሪ የሚደረግላቸው እንግዶች ባሉበት በታላቅ ድምቀት የሚደረግ ሲሆን በዕለቱም ለአሸናፊዎቹ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጁላቸው ሽልማቶች ይበረከቱላቸዋል፡፡

Leave a Comment