ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ባዘጋጀው በነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ነዳያንን በመመገብና ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል።
በቅዱስነታቸው የሚመራው የልዑካን ቡድን በስፍራው ሲደርስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ሲቲ አህገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የማኅበሩ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ፣ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መምህር ኤልያስ ሙላቱና የማኅበሩ አባላት ደማቅና መንፈሳዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
በዚሁ ጊዜም ህጻናት እቅፍ አበባ ያበረከቱ ሲሆን የማኅበሩ ዘማርያንም መንፈሳዊ መዝሙር በመዘመር ከፍተኛ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ማህበሩ በየወሩ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ 5800 ለሚሆኑ ቤተሰቦቹ ቋሚ ድጋፍ ከማድረጉ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ጥር 29/2017 ዓ/ም 10 ሚሊየን ብር በመመደብ የማዕድ ማጋራት ስነ ስርዓት ከማካሄዱ በተጨማሪ 13 ለሚደርሱ አካል ጉደመተኞች የዊልቸር እና 25 ለሚደርሱ ቤተሰቦች ደግሞ ሙሉ የቤት እቃ ድጋፍ አድርጓል።
ኀበመርሀ ግብሩ ላይ ፣ ሁሌ ድጋፍ የሚያደርግላቸው የመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ተወካዮች፣ የባቡል ኸይር መስራች ፣ የሙዳይ በጎ አድራጎት መስራች ፣ የሜሪጆይ መስራች የጌርጌሴኖን መሥራች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሚዲያ አካላት በቦታው ተገኝተዋል።
ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበራት ማደራጃ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን የማኅበራት ምዝገባ መስፈርቶችን በማሟላት ሕጋዊ ዕውቅናና ፈቃድ የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል።





4 comments
🙏🙏🙏❤❤❤
10,000 Mil yemebale kuter ale ende?
ቁጥሩን አስተካክላችሁ ግለጹት!
ለማያውቅሽ ታጠኝ አለ😎😎