0
በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታወቀ።
ከነገ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል።
በለውጡ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 6፡30 የነበረው ከ1፡00 እስከ 5፡30 እንደሚሆን አስታውቀዋል።
እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ9፡00 እስከ 11፡30 የነበረው 10፡00 እስከ 12፡30 እንዲሆን መወሰኑን አቶ ኡቶው አመልክተዋል።
የስራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር አስረድተዋል።
9 comments
Shame Abdi
ጥሩ ለውጥ ነው
Shame Abdi ጥሩ ለውጥ ነው
አላህ ያብርደው ሙቀቱን አብሽሩ🤲
አአምኮ ሙቀት አለ ለምንድነው ጠዋት 4😌 ሰአት ገብተን ማታ 9😳 ሰአት ማንወጣው ጠይቅልን እስቲ🤲
በእዪ ጩፋ ዱዋ ማስደረግ ነው 😎
አቤት የዚች ሀገር ፈተና ፈጣሪ ሆይ በቃችሁ በለን🙏
በጋምቤላ ብቻ መቅረት የለበትም
ከፍተኛ የሆነ የአየር ሁኔታ ለውጥ በመኖሩ ሌላ ቦታዎችም ታሳቢ መደረግ አለባቸው።
ሁመራም በረከቱ ይድረሰን🤔
ጋምቤላ ሲጀምር ሰዎቹ እዚሁ አዲስ አበባ አይደላችሁ እንዴ