0
#FastMereja I ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግል/ማህበር ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም እና ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም ለተለዩት እድለኞች ቅዳሜ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከቃሊቲ ወደ ጋርመንት በሚወስደው መንገድ ባለው ሳይት የማስጎብኘት እና የፎሎር እጣ አውጥቷል።
አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ እና ዝቅተኛ ወርሃዊ ቁጠባ የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሰራው ነው ያለው ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን እየተገነባ የሚገኘው የቃሊቲ ሳይት በአንድ ወለል 10 ላይ ቤቶች የሚገኙ ሲሆን በአጠቃላይ 160 ቤቶች የያዘ ህንፃ እንደሆነ ተገልጿል። ህንፃውን ገንብቶ ሚያዝያ 30/2017 ዓም ለማስረከብ እንደሚሰሩ ገልጿል።
በመርሃ ግብሩ ላይ እስካሁን ያጋጠሙ ችግሮች እና በምን መንገድ እንደተቀረፉ እንዲሁም ወደፊት ለመስራት የታሰቡ እቅዶች ማብራሪያ ተሰጥቷል።




