banner

የግለሰቧ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የልደት ምስል ቀረጻ ከተቋሙ አመራሮች አውቅና ውጪ የተደረገ ነው – አየር መንገዱ

ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር የነበረው የአንዲት ግለሰብ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የልደት ምስል ቀረጻ
ከተቋሙ አመራሮች አውቅና ውጪ የተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አንዲት ግለሰብ በአውሮፕላኑ መወጣጫ ደረጃ ላይ የተለያዩ ዲኮሮችን በማድረግ የተነሳችው ፎቶ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር መታየቱን ገልጿል፡፡

ግለሰቧ የተነሳችው ለጥገና በቆመ አውሮፕላን ላይ መሆኑን የጠቆመው አየር መንገዱ÷ድርጊቱ ከተቋሙ አመራሮች አውቅና ውጪ የተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ የሙያ አገልግሎት ሥነ-ምግባርን በመጠበቅ ደረጃውን የሚመጥን አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ይሁን እንጂ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ተቋሙ ከሙያዊ ሥነ ምግባር ውጪ ገንዘብ በመቀበል ለግለሰቧ ፈቃድ እንደሰጠ በማስመሰል በተሰራጨው መረጃ ማዘኑን አንስቷል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለጸው አየር መንገዱ÷ከተቋሙ አመራሮች አውቅና ውጪ ቀረጻ እንዲካሄድ በፈቀዱ አካላት ላይ አስተዳደራዊ ርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጧል፡፡

Leave a Comment