0
“ባህላዊ እሴቶቻችን ለጠንካራ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የባህል ፌስቲቫል በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በሲዳማ ባህል አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
በፌስቲቫሉ ላይም “Dawooe Bushshu” (ዳዎኤ ቡሹ) ፊልም ተመርቆ ለተመልካቾች ለእይታ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
የሲዳማ “ዳዎኤ ቡሹ” የሰላምታ አሰጣጥ ሥርዓት ለሰላም፣ ለአብሮነት፣ ለዕርቅና ለመቻቻል እንዲሆን በጋራ በሚሰራበት ሂደት ዙሪያ ገንቢ ውይይት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ዳዎኤ ቡሹ” የሲዳማ ሕዝብ እንግዳ ስመጣ በመተቃቀፍ ሰላምታ ከመለዋወጥ ባሻገር በውስጡ ፍቅርን መስጠት ፣ መቀባበልን ፣ የመከባበር እና የአብሮነት ጥልቅ ስሜት የያዘ ድንቅ ባሕል መሆኑንም ቢሮው የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መቆየቱም የሚታወቅ ነው።
የባህል ፌስቲቫሉን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ብሎም ሌሎች ከፍተኛ የክልል አመራሮች በተገኙበት ተከፍቷል።
#FastMereja I #ኹነት





2 comments
Sidaamimma 💚🤍💙
👍👍👍👍👍👍👍🇪🇹