#FastMereja I በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን የተጻፉ እና መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ሁለት አዳዲስ መጽሐፍት ለንባብ ሊበቁ መሆናቸው ተገለጸ። “Walking with Grace: 90 Days Devotional for a Believer’s Journey” እና “እውነተኛ ክርስቲያናዊ ኑሮ፦ የያዕቆብ መልእክት ምጋቤያዊ ትንታኔ” የተሰኙት እነዚህ መጻሕፍት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ9:00 ሰዓት በአዲስ አበባ ኤቨርላስቲንግ ክራይስት ሪቭሌሽን ቤተክርስቲያን እንደሚመረቁ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተገለጸው፣ “እውነተኛ ክርስቲያናዊ ኑሮ፦ የያዕቆብ መልእክት ምጋቤያዊ ትንታኔ” የተሰኘው መጽሐፍ የያዕቆብ መልእክት በኢትዮጵያውያን አማኞች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መሆኑን በማስታወስ፤ መጽሐፉ ከእምነት፣ ከታሪክ፣ ከባህልና ከወቅታዊ ማህበራዊ አስተሳሰብ አንፃር ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በሌላ በኩል “Walking with Grace: 90 Days Devotional for a Believer’s Journey” የተባለው የጽሞና መጽሐፍ አንባብያን ከፈጣሪ ጋር ዕለታዊ የጸሎትና የቃሉን ንባብ ጊዜ እንዲያሳልፉ፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ሕይወታቸውን እንዲያሰላስሉ የሚያግዝ ተግባራዊ መመሪያዎችን የያዘ መሆኑ ተመላክቷል።
የምረቃ ስነ-ሰርዓቱ ንባብን ከሚወዱ እንግዶች፣ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ አገልጋዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እንደሚካሄድ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል።
በተጨማሪም መጽሐፎቹ በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ለሚገኙ አንባቢያን በሀርድ ኮፒ (በህትመት) እንዲሁም በሶፍት ኮፒ በኦንላይን አማራጮች ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ተነግሯል።
#ኹነት





1 comment
ልዩ ዜና ለኦር*ቶ*ዶክስ ኢየሱስ ብቻውን ያድናል ኑ ወደ ኢየሱስ