banner

«ኒው ፌስ ፋሽን ናይት» የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

#FastMereja I ኒው ፌስ ሞዴሊንግ ማኔጅመንት ልዩ የተባለውን «ኒው ፌስ ፋሽን ናይት» የፋሽን ትርዒት የፊታችን እሁድ ህዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ በጃክሮስ አካባቢ በሚገኘው «ቬኑ ዌር ሀውስ» ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ። ተቋሙ ይህንን ይፋ ያደረገው ዝግጅቱን አስመልክቶ ዛሬ በቫምዳስ ሲኒማ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

በመግለጫው ላይ የማሰልጠኛ ተቋሙ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ሞዴል ዮሐንስ ወርቅነህ እንደገለጹት፣ ተቋሙ በዘርፉ አንቱታን ባተረፉ ባለሙያዎች በመታገዝ ሰልጣኞች የመድረክ ጠባቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸው መድረክ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል። ይህንንም እውን ለማድረግ በያዝነው ዓመት በርካታ የፋሽን መድረኮችን ለማዘጋጀት መታቀዱን በቫምዳስ ሲኒማ ከተሰጠው መግለጫ ሰምተናል።

«አዲስ አበባን በፋሽን ዘርፍ ካደጉት ሀገራት ከተሞች እኩል የፋሽን መዲና የማድረግ ታላቅ ራዕይ ሰንቀን እየሰራን ነው» ያሉት ሞዴል ዮሐንስ፣ ዝግጅቶቹን በላቀ ደረጃ ለህዝብ ለማድረስ ከ«ቱራይዝ መልቲሚዲያ» ጋር በሚዲያና ኢቨንቶች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውንም አስታውቀዋል።

በዚህ ልዩ የፋሽን ምሽት ላይ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ባለሀብቶችና የሙያው ቤተሰቦች የሚታደሙ ይሆናል።

#ኹነት




Leave a Comment