banner

ትርታ 97.6 FM ሬድዮ ጣቢያ ባለድርሻዎች የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ተስማሙ

#FastMereja I ትርታ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚያስተዳድረው ትርታ 97.6 FM ሬድዮ ጣቢያ ባለድርሻዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በንግግር ለመፍታት ተስማሙ።

ታህሳስ 2016 ዓ.ም. የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የትርታ 97.6 FM ጣቢያ ባለድርሻዎች ባለፉት ሁለት ወራት ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሰፊ ውይይቶችን በማደረግ የነበሩ ችግሮችን መፍታት የቻሉ ሲሆን፣ በቀጣይም ጣብያውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ጠንከር ያለ ስራ ለመስራት ወስነዋል።

በመጨረሻም ባለድርሻዎቹ በችግሩ ወቅት ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል ።
የትርታ 97.6 ኤፍኤም ታህሳስ 13/2015 ዓም መደበኛ ስርጭቱን መጀመሩ ይታወሳል።

ዘገባው የትርታ 97.6 FM ነው።

1 comment

ዘኒ የጥሩዬ ልጅ February 19, 2025 - 3:57 pm

ጨቆን ነበር🙄

Reply

Leave a Comment