#FastMereja I ከተመሰረተ አንድ አመት ከመንፈቅ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተሞች የተመጠጣነ ዕድገት መምራት የሚችሉ፣ ለኢንቨስትመንት፣ለኑሮም ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ ከተሜነትን በአግባቡና በተቀናጀ ሁኔታ መምራት እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ዘውዴ ገለፁ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ6 ማዕከል በመደራጀቱ ለከተሞች የመልማት ዕድል እንዳመጣ የተናገሩት ኃላፊው በከልሉ ካሉ 248 ከተሞች መሃከል 54ቱ የፈርጅ ለውጥ ሲያገኙ 3 ከተሞች ደግሞ ወደ ሪጂዮ ፖሊስ ከተማነት መሸጋገራቸውን ገልፀዋል፡፡
ይህም የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍታት ፣ የገቢ መጠንን ለማሳደግ እንዲሁም የውሳኔ ስልጣን በመጨመር ለነዋሪው የሚመጥን አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡
ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ ማለት በክልል የመጀመሪያ ደረጃ ከተማ ማለት ነው ያሉት አቶ ብርሃኑ በዚህም በክልሉ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭና ዲላ ከተሞች ወደዚህ ፈርጅ ያደጉ ከተሞች መሆናቸውንም አቶ አብራርተዋል።
ከአስተዳደር አንፃርም ዞኑ ላይ የነበረው ጫና በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ገልፀው የመወሰን ስልጣናቸውንም እንደሚጨምርላቸውም አብራርተዋል።
በክልሉ በአጠቃላይ 54 ከተሞች የፈርጅ ለዉጥ ማድረጋቸውን የተናገሩት አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከዚህ ዉስጥ 11 ከተሞች ወደ ፈርጅ ሶስት፣ 5 ከተሞች ወደ ፈርጅ ሁለት፣ 5 ከተሞች ወደ ፈርጅ አንድ፣ 8 ከተሞች ከፈርጅ አምስት ወደ ፈርጅ አራት እንዲሁም ፈርጅ ያልነበራቸው 22 ከተሞች ወደ ፈርጅ አምስት ሽግግር ማድረጋቸውን አስረድተዋል።
ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ህዘቡ ህጋዊ በሆነ መንገድ ባለይዞታ እንዲሆን የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት በማህበራት ማደራጀትና በሊዝ እንዲቀርብ እየተደረገ ሲሆን በማዘጋጃ ቤት አከባቢ ያለውን ክፍተት ለማስተካከልና ለማዘመን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ከተሞች የችግርና የጉስቁልና ማሳያ ሳይሆኑ የልማትና የብልፅግና ምሳሌ፣ ሰዎች በደስታ የሚኖሩበት እንዲሆኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተሞች የሰላምና የመቻቻል ደሴት፣ኢትዮጵዊ መልክ የያዙ፣ በተፍጥሮ ሀብት፣ በሰላም አምባሳደርነት በቱሪዝም መዳረሻነት የሚቀጥሉ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነፃነት የሚኖርበትና የሚያለማበት የብልጽግና ተምሳሌት ሆነው እንዲሚቀጥሉ አቶ ብርሀኑ ዘውዴ ተናግሯል።
#ማህበራዊ

3 comments
Brish Zewdie
Berhanu Zewdie Zeta ትችላለህ
ሪጂዬ ፍሪኝ 😥😥 😭😭ማላቀው እኔ 🤔🤔🤔ግን ምን ማለት ነው
የ ፈርጅ ለውጥ 🤔🥴