#FastMereja I Grand Ethio–Africa Run በዱባይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ እንደሆነ ዛሬ የካቲት 28/2017 ዓም በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲሁም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የስፖርት ፋሽን ባህልን ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ነው የተባለለት ውድድሩ FAS Business Group ከዱባይ ስፖርት ካውንስል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን የዲፕሎማሲ ፣ ባህል እና ስፖርት ግንኙነቶችን በማስተሳሰር መልካም መስተጋብርን ለመፈጠር የሚያስችል ታሪካዊ ትዕይንት እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጿል።
ሚያዚያ 6 ቀን 2025 ደግሞ የGrand Ethio-Africa Run በዱባይ የሚካሄድ ሲሆን በዚህ ልዩ ዝግጅት ከአፍሪካ፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንዲሁም አለም አቀፍ ተሳታፊዎችን በጋራ ያጣመረ ሩጫ ወድድር ይደረጋል።
ከሚያዝያ 5 የሚጀምረው ዝግጅቱ የባህላዊ ዘመናዊ በዲጄ የታጀበ የዳንስ እንቅስቃሴዎች የሚታዩበት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የባህል ጭፈራዎች የሚቀርቡበት ልዩ የመዝናኛ ትዕይንትም ተዘጋጀቷል።
መርሃ – ግበሩ የዲያስፖራውን ማህበረሰብ በኢንቨስትመንት፣ ባህል እና መዝናኛ ፕሮግራሞች በማሰባሰብ የሚቀጥል ወርሃዊ ዝግጅት እንደሆነም በመድረኩ ተጠቁሟል።




