banner

በዛሬው እለት ከ24 ድርጅቶች እና 3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000 ብር መቅጣቱን ገለፀ።

#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 1,800,000 ብር፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,750,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1,200,000 ብር፣በጉለሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

በተያያዘ ዜና በቦሌ ክ/ከተማ 450,000 ብር በኮልፌ ክ/ከተማ 400,000 ብር ፤በልደታ ክፍለ ከተማ 100,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ለመንግስት ገቢ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት 24 ጅርጅቶች እና 3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገልጿል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

9 comments

ሶሊ ያና March 12, 2025 - 7:02 pm

ለሜቄዶንያ ስጡ ይሄን ብር

Reply
Meku Ethiopia March 12, 2025 - 7:03 pm

ወጭዉን እኛ ነና ምንከፍለዉ ማለት ነው አይ ህዝቤ😂

Reply
Mifta Arebo March 12, 2025 - 7:04 pm

የሰው ልጅ ቅጣት ብቻ አያስተምረውም
በምክርም እንዲማር ማድረግ ያስፈልጋል።😕

Reply
Enuka Kulche March 12, 2025 - 7:05 pm

ለአብይ ልጅ ለነገ ቁርስ ችሏል🤗😌

Reply
Kusse Bedenta March 12, 2025 - 7:05 pm

ግድ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በቅጣት ብቻ ነው የሚማረው።

Reply
Sultan Nuri March 12, 2025 - 7:05 pm

Men beytfue nwe

Reply
Abu Adilah March 12, 2025 - 7:06 pm

አንቺም ዜሮ ዜሮ እኔም ዜሮ ዜሮ እውይ ዘንድሮ

Reply
Háymi Wedajo March 12, 2025 - 7:06 pm

ይኼ መንግስት ግን😂ባያበድር ይገርመኛል 🔥

Reply
Ep Bin March 12, 2025 - 7:06 pm

በ 1 ቀን 6.7 ሚሊዮን ብር እረ ያንሳል💀

Reply

Leave a Comment