#FastMereja I የኢትዮጵያ የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የሁለቱን ሃይማኖት አፅዋማት መግባት ተከትሎ የደምና የደም ተዋፅም አቅርቦት እንዳይስተጓጎል ከሚዲያ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት አድርጓል።
በመጋቢት ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የደም ማሰባሰብ ንቅናቄ 55 ሺሕ ዩኒት ደም እንዲሁም በአዲስ አበባ ደግሞ 15 ሺሕ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን የኢትዮጵያ የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋ/ዳይሬክተር አቶ ሐብታሙ ታዬ አስታውቋል።
ንቅናቄው እንዲካሄድ ምክንያት የሆነው የእስልምና እና የክርስትና ተከታዮች ፆም በተመሳሳይ ወቅት ላይ መግባቱን ተከትሎ፤ የደም ለጋሽ ቁጥር ስለሚቀንስ እጥረት እንዳይፈጠር ለማድረግ በመታሰቡ ነው ተብሏል።
“መጋቢት ወር የደም ልገሳ ወር” በሚል ንቅናቄ እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ በጎ ፍቃድ ደም እንዲለገስ ተቋሙ ጥሪ አቅርቧል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ ከሚዲያ ተቋማት የተወከሉ ባለሞያዎች እና የኮሙኒኬሽን ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ የዐይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል ገብተው ፊርማቸውን አኑሯል።
የዐይን ብሌን የሚለግሱ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

10 comments
ሰዎችን እንዳያችሁ እኔ ያሰብሁትን ካሰባችሁ ሲዖል እንገናኝ😀
በሽያጭ ወይስ በነፃ?😊
ይሄኔ ኮ አያይም
እኔ ራሱ ሀሳቡ አለኝ ❤
ጋዘጠኛ ምን ዐይን አለው? ባይሆን ምላስ አለው። አድርባይ ምላስ ።
እኔም ከሀይማኖት አኳያ ይፈቀዳል ወይ የሚለው ነገር አጣርቼ እንለግሳለን
የፈለጉትን ያክል ፃድቅ ብሆኑም; እግዚአብሔር በፈጠረው ሙሉ አካላዊ ጉድለት በሀጥያትን ልጠየቁ ይችላሉ።
ተሸዉዶ አራዳ ሁላ😷😷😷
ከሀገር ሲወጡ እንዴት ሊያደርጉ ነው
የማይሰደዱት ከሆነ ጥሩ ነው
ነበራቸው እንዴ🤔