0
#FastMereja I “በትዳር ውስጥ እንዴት እንኑር?” የተሰኘው በወ/ሮ ሒሩት ዳንኤል የተፃፈው መፅሐፍ ሊመረቅ ነው።
መኖሪያቸውን በእንግሊዝ ሀገር ካደረጉ 40 አመታት ያስቆጠሩት ወ/ሮ ሂሩት መጋቢት 13/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳርቤት መካነ ኢየሱስ በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ የስልጠና ማዕከል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።
በጋብቻ ውስጥ 40 አመት ማስቆጠራቸውን የገለፁት ወ/ሮ ሂሩት “ጋብቻ መልካም ነው የእግዚዓብሔር በረከት ነው” ብለዋል ከራሳቸው ትዳር ተሞክሮ እና ከሌሎች የተመለከቱትን አካተው እየተበራከተ የመጣውን ፍቺ እንዴት መቀነስ እንደሚቻል በትዳር ውስጥ እንዴት እንደሚኖር የሚገልፅ መፅሐፍ እንደሆነ ገልጿል።
ወይዘሮ ሂሩት የሁለት ልጆች እናት ሲሆኑ ሁለት የልጅ ልጆች ማየት ችሏል።
“በትዳር እንዴት እንኑር?” መፅሐፍ በ232 ገፅ ብዛት የቀረበ ሲሆን፣ በ450 የኢትዮጵያ ብር ይሸጣል። መካነ ኢየሱስ መፅሐፍት መደብር ውስጥ ይገኛል።



4 comments
ወ/ሮ ሂሩት ራሱ ተፋተዋል
ኢየሱስ የሚለውን ብቻ አንብቦ ሊፈረጥጥ የተዘጋጀ የኢየሱስ ጠላት ቢኖር ጥላቻው የፈረሰ ይሁን🙏
ይሄኔ ጸሃፊዋ እራሷ ትዳር የላትም።🤣
I have that book but I haven’t wife