#FastMereja I ብርቱካን ተወልዳ ያደገችው ም/ጎጃም ስናን ወረዳ ነው። ብርቱካን አባቷ መሰደዱን እና እናት በወሊድ ምክንያት ህይወቷ ማለፉን ትናገራለች።
ፋስት መረጃ ከቃለምልልሱ እንደተመለከተው ብርቱካን እስከ 8 አመት አያቷ ጋር ካደገች በኋላ የሰው ቤት ገብታ እየሰራች ትምህርቷን እየተማረች ነበር፣ እስከ 8ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪ በመሆን የተሸለመችው ብርቱካን ቤት ውስጥ ከምትሰራው ከባድ ስራ ጎንለጎን ትምህርቷን ቀጥላ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ወስዳ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ ዲፓርትመንት ትምህርቷን ጀመረች።
በዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆነች ምሽት ከላይብረሪ ስትመለስ በግቢ ውስጥ ረብሻ ተከሰተ የምትለው ብርቱካን ከውስጥም ከውጪም ተኩስ ነበር ቶሎ አምልጡ በማለት እዚህ መኪና ግቡ ብለው ይዘውን ጫካ ገቡ ብላለች።
የፈልግናችሁ ለስልጠና ነው አብራችሁን ትሆናላችሁ ብለውን ጫካ አስቀመጡን በጣም የመከራ ጊዜ ነበር የሚበላ የሚጠጣ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር ትላለች ብርቱካን ጊዜው ሄደ አመት ከስድስት ወር ተቆጠረ «አሁን ስራችንን እንጀምር» በማለት ሁላችንንም ልብስ አስወልቀው አሰለፉን እኔ ስድስተኛ ነበርኩ እየተፈራረቁ ነበር የሚደፈሩን ከዛ በኋላ ሰውነቴ ደንዝዟል በፌሮ ይወጉት ነበር ብላለች።
በስድስተኛ ቀኔ ስነቃ ደም እየፈሰሰ ነበር፣ ነገ ህይወቴ ይለወጣል፣ ነገ ጥሩ ቦታ እደርሳለሁ ያልኩት ልጅ መጨረሻው እንደዚህ ሲሆን በጣም ከፋኝ፣ ህይወቴን በምን መልኩ ነው የምቀጥለው፣ አይዞሽ የሚለኝ ሰው የለኝም። መጨረሻ ላይ የጎዳና ተዳዳሪ ነው የሆንኩት ብላለች።
ከተደፈረች በኋላ በማርገዟ ልጅ ወልዳለች፣ እሷም ታማሚ ናት፣ መለወጥ መደገፍ ህይወቷ ድጋሚ እንዲለመልም ተስፋ እንዲኖራት ትፈልጋለች።
ብርቱካን ከኢቢኤስ ጋር በነበራት ቆይታ።

9 comments
እግዚአብሔር አምላክ ያበርታሽ
ከዚህ በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር ይኖራል!!!😭
Ay faNo 💔
አውሬዎች ናቸው!
ቅድስ ሀገር ኢትዮጵያዊያን ካሜራ ያልስማሁ ብዙ ጉድ አለ
ሰው ከዝንጀሮ መፈጠሩን ያረጋገጥኩበት! አፈር ነውና ወደ አፈር ይመለሳሉ የሚለውን “ዝንጀሮ ነውና ወደ ዝንጀሮ ይመለሳሉ” አልኩኝ
የባንዳ ልሳን የተወለደችበትን እንደጠቀስክ ዩኒቨርስቲውንም ጥቀስ
ሰው የታጣባት ሀገር‼️😭😭
ያልገባኝ video ከ YouTube የጠፋበት ምክንያት ነው ሙሉው ያላችሁ በውስጥ ብታጋሩኝ ደስስ ይለኛል!