0
#FastMereja I የወንጌል አርበኛ የነበሩት አባባ ባንጫ ያያ “ቃለ ሕይወት” የሚለውን ስያሜ የሰጡ እና አባባ ባንጫ ያያ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ዋና ፕረዝዳንትም ነበሩ።
አባባ ባንጫ የተወለዱት በዎላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሞኮኒሳ ወይጌ ቀበሌ ነበር።
አባባ ባንጫ ያያ “ቃለ ሕይወት” የሚለውን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጥተዋል። እንዲሁም “ወልድ ያለው ሕይወት አለው” የሚለዉ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መሪቃል በተከፈተ መጽሐፍ ላይ “logo” ወይም አርማ እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀሳብ የሰጡም ናቸው።
አባባ ባንጫ በዎላይታ ቀጣና የጫራቄን ክፍለ ማህበርን ከ 40 ዓመታት በላይ በዋና ጸሐፊነት አገልግለዋል። ከእርሳቸው በኋላ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻሉ የወንጌል አርበኛ አባቶች እነ ሾንጋንና ዳልኬ የመሳሰሉትን የሰበኩ እና የጠመቁም ነበሩ።
አባባ ባንጫ በተወለዱ በ137 ዓመታቸው ማረፋቸውን ከካውንስሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

6 comments
እምነቱንኮ በእድሜ እሳቸው ይበልጡታል🤔
መልካም እረፍት 🙏
Rip
ቃለ ህይወት የሚለውን ቃል
ትርጉም እንዴት አወቁት
RIP😭
ወደ አገለገሉት ጌታ በክብር ተጠርቷል👏👏