banner

አዋሽ ባንክ በ100 ከተሞች የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የ63 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

#FastMereja I አዋሽ ባንክ የ2017 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

በዛሬው እለት በአራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቅጥር ግቢ በተዘጋጀ መርሃ ግብር አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ ከ100 በላይ በሚሆኑ የድጋፍ መስጫ ጣቢያዎች ከአስር ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን እና ሌሎች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለበዓሉ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ገልጿል።

አዋሽ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በመንግስትና በማህበረሰቡ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን በመደገፍ ረገድ የበኩልን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በተያያዘም ባንኩ የ1446ኛዉን የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ከተሞች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ለሙስሊም ወገኖች ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡





2 comments

Libsnew Salelh April 14, 2025 - 8:38 am

tarkawi bank new 10q debrtabor seste selayew endezeh yalewn banke yasefalen

Reply
Ethiopia Yehulachin Nat April 14, 2025 - 8:38 am

ሹፍ እንግዲ ይገቡና የከተማው ስም ይጠቀስ

Reply

Leave a Comment