banner

ትላቅ የሬሳ ሳጥን ተሰርቶ ጥላቻ በአዲስ አበባ የሚቀበርበት ሁነት የጥላቻ ቀበራ ሊዘጋጅ ነው!

#FastMereja I ያሜንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በቀጣይ የሚያከናውናቸውን ፕሮጀክቶች በዝርዝር ካሳወቀ በኋላ ከፊኒክስ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር የአጋርነት ፊርማ ተፈራርመዋል።

ያሜንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት፣ በሀገራችን ያሉ የቤተሰብ ምስረታ የጋብቻ ሁነቶች ላይ ጥናት በማድረግና ቤተሰብ በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ድርሻ ግምት ውስጥ በማስገባት ”ቤተሰብን መመስረት ሀገርን መገንባት ነው” በሚል መሪ ቃል ባለፉት አመታት ሶስት የየሺህ ጋብቻ ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ በደማቅ የጀማ ሰርግ ውጤታማ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ያሜንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የየሺህ ጋብቻ ስራዎችን መሠረት በማድረግ፣ የተገኙ ልምዶችን በመቀመር እና የስራ አድማሱን በማስፋት የያሜንት ፕሮጀክቶችን በተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ በማቀድ የማህበረሰቡን ችግሮች በፈጠራ ላይ በተመሰረተ የማህበረሰብ ተሣትፎ መፍታት በሚለው የማህበራዊ ጉዳዮች አቅጣጫ መሠረት ለማከናወን እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጧል።፡

ያሜንት የተሰማራባቸው የሥራ ዘርፎች፡-

1- የሺህ ጋብቻ –

ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙሽሮች የሚሣተፉበትን የሰርግ ስነስርዓት በማዘጋጀት የሚታወቅ ማህበራዊ ሁነት ሲሆን የሙሽሮችን የሰርግ ወጪዎች በማስቀረት ደማቅና አይረሴ የሰርግ፣ የካርኒቫልና ኤክስፖ ሁነቶችን በማዘጋጀት ባህላዊ ጋብቻዎችን ያበረታታል፣ ለቱሪዝም ዘርፍ እድገትና ለህዝቦች አንድነት መጠናከር የበኩሉን ኢኮኖሚያዊ ሚና ይጫወታል፡፡ በውጤቱም ተጋቢ ጥንዶችን፣ ቤተሰቦቻቸውን ባህላዊ ጋብቻ ስርዓትን፤ የሰርግ ስነስርዓት አዘጋጆችንና፣ በባህል አልባሳትና ጌጣጌጥ ምርትና አገልግሎት የተሰማሩ ዜጎችንና በአጠቃላይ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ የሚቀጥለው የሺህ ጋብቻ ሁነት ጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ወደፊትም ተጠናክሮ በየዓመቱ ይቀጥላል።

2- የሺህ በዓል ፡-

ያሜንት ትዳር የመሰረቱና በትዳር ህይወት ውስጥ ያሉ ባለትዳሮች በጋራ የሚያከብሯቸውን የተለያዩ በዓላት በማዘጋጀት ማህበራዊ ሁነቶችን ያስተባብራል፡፡ በዚህም የቤተሰብ ግንኙነቶችን ያጠናክራል፣ በሀገር አቀፍና በክልሎች ተመሳሳይኩነቶችንያዘጋጃል፡፡ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ መግባባትና የህዝቦችን አንድነት ከፍ የማድረጉ ተግባራትን ይፈፅማል፡፡ ይህ ዝግጅት ሙሽሮች፣ ቤተሰቦች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና መላው ህብረተሰብን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ይህ በዓል ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በዓል የሚያከብሩበት ሁነት ይሆናል፡፡

3 ጥላቻ ቀበራ

የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ህይወት የተመለከቱ የሰላምና የደህንነት ዕሴቶችን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ክንዋኔዎችን በማስተባበርና ተሣትፎውን ለማጠናከር የሚያግዙ ህብረተሰባዊ የአንድነት ትስስር በመፍጠር የጥላቻ ቀበራ ሀገር አቀፍ ሁነቶችን ያዘጋጃል፡፡ በዚህ ሁነት የህዝቡን በሰላም አብሮ የመኖር ግንዛቤን በማዳበርና የሰላማዊነት መንፈስ በማጠናከር በማያቋርጥ ዕድገት ላይ የተመሰረተ የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር አምራች ዜጋን በማበርታት ሂደት የበኩሉን ድርሻ ይወጣል፡፡ ይህ ሁነት ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከናወን ነው፡፡

በነዚህ ሁነቶች ዝግጅቶች ያሜንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቤተሰቦች፣ የቢዝነስ ድርጅቶች፣ የሰላም ተቋማትና ማህበረሰቡ፣ በሀገሪቱ ዘላቂ የልማት ግቦችና የዕድገት ስትራቴጅ አቅጣጫዎች ተሳታፊነቱን በማጠናከር ከሁለንተናዊ የዕድገት በረከቶች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታዎች ያመላክታል፡፡

የያሜንት ፕሮጀክቶች እየተጠናከሩና ለመጪው ትውልድ ተስፋን እየፈነጥቁ ሁለገብ ማህበራዊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ታላላቅ ግቦችን እያስቀመጡና በተግባር እየተፈፀሙ ይቀጥላሉ። በዚሁ ጎን ለጎን ያሜንት ከራዕዮቹ አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያ ቤተሰብ ማዕከልን የመገንባት ዕቅድ ይዞ የሚያከናወን ይሆናል፡፡

ያሜንት እነዚህን ሁለገብ ማህበራዊ ፕሮጀክቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበርማህበረሰባዊ ችግሮችን በፈጠራ፣ በአካታችነት፣ በአሳታፊነት, በማህበረሰባዊ ተነሳሽነትና ተሣትፎ የመፍታት አቅጣጫን በተከተለ መንገድ ይሰራል፡፡ በዚህ አሰራርም የማህበረሰቡን መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት፣ አገር በቀል ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማጠናከርና የህብረተሰብ ተግባቦትን ለመፍጠር በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል።





5 comments

Da Wit April 16, 2025 - 4:06 pm

በቁሜ ውስጡ ባስገቡኝ

Reply
Xavier replies በአማርኛ April 16, 2025 - 4:08 pm

አድስአበባ ዝር አልልም

Reply
Abdu Mohammed April 16, 2025 - 4:08 pm

ብዙ ስለሆኑ ትንሽ ሰፋ ቢያረጉት

Reply
Mêqüanint Gödö April 16, 2025 - 4:08 pm

ስነስርዓቱ ላይ ሲኦል ያሉ ሰዎች በእንግድነት ቢገኙ!😁

Reply
ሙሉ ጎጃም April 16, 2025 - 4:09 pm

ይሄን እቃ እቃ ጨዋታችሁን ብትተው ምን አለበት

Reply

Leave a Comment