banner

ሁለት ህፃናት ከታገቱበት በፖሊስ ክትትል ወደ ቤተሰብ ተመልሷል።

#FastMereja I ከእንሴኖ ከተማ አስተዳደር የታግተው ህፃን ህዝቄኤል አሳምነው በቢሾፍቱ ከተማ ከነሙሉ ጤንነቱ ተይዞ ወደ ቤተሰቦቹ መቀላቀሉን የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል አስታወቁ።

ህፃን ህዝቄኤል አሳምነው ከሚኖርበት እንሴኖ ከተማ 02 ቀበሌ በቀን 8/08/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰዓት በመኖሪያ ቤቱ ታግቶ መወሰዱ አስታውሰዋል።

ህፃኑን ያገተው ተጠርጣሪ የወላጆቹን ቤት ተከራይቶ ይኖር የነበረው አቶ ሳሙኤል ደስታ በሀሰተኛ ስሙ ፊሊሞን ሰለሞን ሲሆን ወደ ቢሾፍቱ ከተማ በመውሰድ ተባባሪ ተጠርጣሪ ህይወት ተስፋዬ ቤት ህፃኑን 09/08/2017 ዓ.ም ተይዞ በሙሉ ጤንነቱ ወደ ቤተሰቦቹ መቀላቀሉን ተናግረዋል ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከእንሴኖ ከተማ አስተዳደርና እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ባደረገዉ ብርቱ እና እልህ አስጨራሽ ክትትል በጂፒኤስ በመታገዝ ህፃኑ ሊገኝ መቻሉን ገልፀዋል።

ተጠርጣሪ አቶ ሳሙኤል ደስታ የተሰወረና በክትትል ላይ የሚገኝ ሲሆን ተባባሪ ተጠርጣሪ ህይወት ተስፋ በቁጥጥር ስር ዉላ ምርመራው በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልፅዋል ።

በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ሶዶ ወረዳ ጎጌቲ 3 ቀበሌ በቀን 27/07/2017 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ ማቲያስ ደሳለኝ የተባለ የ8 ዓመት ታዳጊ በተጠርጣሪ አገኘዉ አለሙ መታገቱን አስታውሰዋል ።

በዚሁ ቀበሌ በገበሬነት ተቀጥሮ ለ13 ቀናት ከቆየ በኋላ ታዳጊውን በማገት ወደ ኦሮሚያ ክልል ልዩ ቦታዉ ጫንዱ በተባለ ቦታ ከሸሸገዉ በኋላ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ባደረገዉ ብርቱ እና እልህ አስጨራሽ ክትትል በቀን 03/08/2017 ዓ.ም ታዳጊዉን ከሸሸገበት የግለሰቦች መኖሪያ ቤት ሊገኝ ችሏል።

ተጠርጣሪ ለጊዜዉ የተሰወረ ሲሆን አሁንም በክትትል ላይ ይገኛል። በዋናነት ታዳጊዉን በማሳገት የተጠረጠረዉ መስፍን ፈቀደ በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራው በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልፅዋል ።

ተጠርጣሪዎቹ ድርጊቱን እየፈፀሙ ያሉት አግተው ከቤተሰቦቻቸው ብር ለመቀበል ስለሆነ ህብረተሰቡ ቤት ሲያከራይም ሆነ ለማንኛውም ስራ ሰራተኛ ሲቀጥር አስፈላጊውን የአከራይ ተከራይ ውል በመፈፀምና አስተማማኝ ተያዥ እንዲያቀርቡ በማድረግ እራሱን ከአደጋ እንዲከላከል ተገልፆዋል ።

ታጋቾቹ እንዲገኙና ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ብርቱ ክትትል ላደረጉ የኦሮሚያ እና የዞኑ ፖሊስ አባላት በመምሪያው ስም አመስግነዋል መረጃውን እንሴኖ ወረዳ ነው ያገኘነው።



Leave a Comment