banner

ቤቲ ኢንተርናሽናል ሜካፕ ስኩል ተማሪዎቹን አስመረቀ

#FastMereja I ቤቲ ኢንተርናሽናል ሜካፕ ስኩል በሜካፕ፣ በጥፍር እና በአይላሽ እንዲሁም በፀጉር ስራ ከ3 ወር እስከ 6 ወር ያሰለጠናቸውን ከ125 በላይ ተማሪዎች በ17ኛ ዙር ዛሬ ሚያዝያ 23/2017 ዓም በኤልሶል ሆቴል አስመርቋል።

ቤቲ ኢንተርናሽናል ሜካፕ ስኩል ከተመሰረተ 8 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በማስተማሩ አራት አመታት አስቆጥሯል።

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በአዳማ በሚገኘው ቅርጫፉ በአራት አመታት ውስጥ ከ3000 በላይ ተማሪዎች ያስመርቅና ወደ ስራ ያስገባ ድርጅት ነው።

የቤቲ ኢንተርናሽናል ሜካፕ ስኩል መስራች እና ባለቤት ወ/ሮ ቤተል አብይ ባደረገችው ንግግር ተማሪዎቻችን ከራሳቸው የውበት ሳሎን ከፍተው መስራት ለማይችሉ ደንበኞቻቸውን ይዘው በመምጣት የእኛን የውበት ሳሎን መጠቀም ይችላሉ በማለት ለተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

በተጨማሪም ከፈለው መማር የሚያችሉ ተማሪዎችን 50% የዋጋ ቅናሽ በማድረግና ነፃ የትምህርት እድል እየሰጠ ተማሪዎችን አስመርቋል።





Leave a Comment