#FastMereja I ኪነት ኢንተርቴመንት እና ፍካት ኤቨንት እና ዲኮር የድምጻዊት ዘቢባ ግርማ “እንደምንም የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሟን ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
ይህ “እንደምንም የተሰኘው አልበም በግጥም ይልማ ገብረአብ፣ ሞገስ ተካ፣ አለምጸሀይ ወዳጆ፣ መስለ ጌታሁን፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ ወንደሰን ይሁብ፣ ፍሬዘር አበበወርቅ፣ እልፍአግድ እምሻው፤ ኒና ግርማ፤ ገዳ ሀምዳ በግጥም የተሳተፉ ሲሆን
በዜማ ደግሞ አበበ ብርሃኔ ፣ ሞገስ ተካ፣ ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎ፣ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፤ አንተነህ ወራሽ፣ ምህረትአብ ደስታ፤ ካሙዙ ካሳ፣ ዳንኤል ዘውዱ (ዳኒ ቀዮ)፣ አብዲ ያሲን
በመዚቃ ቅንብር አቤል ጳውሎስ፣ ታምሩ አማረ፣ ሸካሙዙ ካሳ፣ ፋኑ ጊዳቦ፣ አዲስ ፍቃዱ ማስተሪንግ ክሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡
ተወዳጇ ድምጻዊት ዘቢባ ግርማ የኛ በሚባል ቡድን ውስጥ በሙዚቃ ስራዋና በትወና ብቃቷ እንዲሁም በመጀመሪያ ነጠላ ዜማዋ ገራገራ በተሰኘው ሙዚቃ እና በርከት ባሉ ነጠላ ዜማዎችን በመስራት ተወዳጅነትን አትርፋለች፡፡
ድምጻዊት ዘቢባ ግርማ ከሀገራች በርካታ ወጣት ድምጻዊያን ጋር ሙዚቃን አብሮ በመስራት በህዝብ ዘንድ እውቅናን ተወዳጅነትነ አግኝታለች፡፡
“እንደምንም” አልበም 13 ሙዚቃዎች ያሉት ሲሆን አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 5 ዓመት እና 5,700,000 /አምስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺ ብር/ በላይ ወጪ እንደሆነበት ተነግሯል።
አልበሙ ላይ ሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ዘቢባ ግርማ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡
“እንደምንም” አልበም ስለ ፍቅር፤ ስለ ምስጋና እና ስለ እናት እና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ይዳስሳል።
“እንደምንም” የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት አንድ በዘቢባ ግርማ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ይገኛል፡፡
#ኪነ_ጥበብ





10 comments
Wechiw ansual !!
እዛው ይቆይልን Please 🙏
5.7 የመሬት መንቀጥቀጥ ነዉ በሉኝ እረ 🥱😁
ኧረ ስለፈጠራችሁ ተውን ግንቦት 1 የእናታችን የድንግል ማርያም ልደት ነው ✝️✝️✝️✝️❤❤❤
ዘፈኑ ምን የሚል ነው 😁😁🙄🙄
ይሄ ሁሉ ብር የወጣበት 😭😭😭😭
በኮሜት ልዝናና
7.5 mil ይገርማል
የቀለደችው መሆን አለበት
ዜማ ላይ ካሙዙ ካለቃው ወደ መንዙማ ተቀየረማለትነው
ትርፉ ስንት ሊሆን ነው 🤔
ምናባቷ ሁና ነው በግንቦት ልደታ ቀን የምትለቀው