#FastMereja I ኢትዮ ቴሌኮም የሀገራችንን የግብይት ሥርዓት በማዘመን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል፣ አካታች ምርት እና አገልግሎት አቅራቢዎችን ከሸማቾች የሚያገናኝ «ዘመን ገበያ» የተሰኘ የዲጂታል ገበያ በይፋ አስጀመረ።
ይህ የዲጂታል ገበያ ለሀገራችን አዲስ ምዕራፍ የምናበስርበት፣ ፈጠራ እና ሁሉን አቀፍ ዕድገትን ለሁሉም ዜጎች ለማድረስ መሰረት የሚጥል በተለይም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ከሸማቾች ጋር በቀላሉ ለማገናኘት፣ ለማብቃት እና አዳዲስ የገበያ እድል በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚን ትሩፋት አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል እንደሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አድፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በማብሰሪያ ፕሮግራሙ ላይ ባደረገችው ንግግር ገልፃለች።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አምጪ የዲጂታል ገበያ ለመሆን በማለም ለሀገሪቱና በኢኮኖሚዋ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ተዋናዮች በማገናኘት ጉልህ ፋይዳ ያበረክታል የተባለለት ዘመን ገበያ በከተሞችና በገጠር ያሉ ሸማቾች ሰፊ የምርት እና አገልግሎት አማራጭ እንዲኖራቸው፣ ምቹና ተደራሽ አገልግሎት ለማግኘት፣ በተወዳዳሪ ዋጋ እና ደህንነቱ በተጠበቀ የዲጂታል ክፍያ አማራጭ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።
ዘመን ገበያ ለደንበኞች በቴሌብር ሱፐርአፕ ውስጥ በሚገኝ ሚኒአፕ አማካይነት የቀረበ ሲሆን፣ የነጋዴዎች ፖርታል እና ሞባይል መተግበሪያ፣ የሸማቾች ሞባይል መተግበሪያ፣ የሎጂስቲክስ አስተዳደር ሥርዓት፣ የላኪዎች (Dispatcher) ሞባይል መተግበሪያ እና የሲስተም አድሚንስትሬሽን ፖርታል አሉት።
ከዘመን ገበያ ጋር በአጋርነት ለመስራት የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከ42 በላይ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ሰጭዎች አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ በቀጣይም ከዘመን ገበያ ጋር በአጋርነት በመስራት የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ወደፊት በማራመድ ጉዞ ውስጥ የበኩላቸውን ለማበርከት ለሚፈጉ በመላ ሀገራችን ለሚገኙ የንግድ ድርጅቶች እና የሎጂስቲክ አገልግሎት ሰጭዎች ጥሪ ቀርቧል።
#ቢዝነስ





3 comments
ዘመን ባንክ በለው ያው ነው የገንዘብ ግብይት ነው
አይ FastMereja ስንት ነገር ስታወሩ የምትውሉት ለመሆኑ ለጤና ባለሙያዎች አንድም ድምጽ ያላሰማች ሁ ምን ይሆን ከ አብይ ማስጠንቀቂያ ተሰጣች ሁ አይደል ይሁን
ሌላ መታለቢያ አመጣችሁ እንታለባለን😂😂