0
#FastMereja I ዛሬ ሚያዝያ 30/2017 ዓም በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የኪ ሃውሲንግ የቤት እድለኞች መለያ መርሐግብር ተመዝጋቢዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
ዛሬ በተካሄደው 4ኛ ዙር እጣ መርሃ ግብር ከሶስቱም ዙር የተመዘገቡ የተካተቱበት ሲሆን በእለቱም 174 ቤቶች እጣ ወጥቷል።
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን Key-CHF የተሰኘ ሞዴል ቀርፆ በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ለ100,000 ቤት ፈላጊዎች በሞዴሉ መሰረት በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች ላይ ግንባታቸው በወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች የተጠናቀቁ ቤቶችን ከአልሚዎች ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት በመግባት በአመት ሁለት ጊዜ እድለኞችን በዕጣ በመለየት የቤት ለማድረግ እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑ ተገልጿል።




