banner

የአንበሳ አውቶቢስ 5ሺ ብር ተቀጣ

#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በለገሀር አከባቢ የከተማ አውቶቢስ ሹፌር ከመኪናው የጠረገውን ደረቅ ቆሻሻን አስፓልት ላይ በመጣሉ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት አምስት ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን አስታወቀ ።

ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በጊዜው ተሸከርካሪዉን ይዞ ከቦታዉ ቢሰወርም በተደረገዉ ክትትል በዛሬዉ እለት የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ላይ ሹፌሩን ከነተሸከርካሪው በቁጥጥር ሰር በማዋል መንገድ በማቆሸሸ ለተላለፈዉ የደንብ ጥሰት የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

Leave a Comment