0
#FastMereja I ለአንጋፋው የስልጥኛ ድምጻዊና የስልጤ ህዝብ የማንነት ታጋይ መሐመድ ስርጋጋ አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሃብት ዘመናዊ የቤት መኪና ስጦታ አበርክቶለታል።
ባለሃብቱ ስጦታውን በህይወት በሌለችው ተጋይ እናቱ ስም ያበረከተ ሲሆን ስጦታው አርቲስትና ታጋይ መሐመድ ስርጋጋ የስልጤን ሁለንተናዊ የማንነት መገለጫዎች ከፍ ለማድረግ ለሰራቸው ዘመን ተሸጋሪ የጥበብ ስራዎችና በማንነት ትግሉ ላይ ላኖረው ደማቅ አሻራ የተበረከተ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
ባለሃብቱ ስጦታውን የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የዞን የስራ ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማስረከቡ ታውቋል።
ሽልማቱ ሌሎች የማህበረሰቡ ተወላጆች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለህዝብ ጠቃሚ አሻራ እንዲያኖሩ የሚያነሳሳ መሆኑም ተጠቁሟል ሲል የስልጤ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

9 comments
ምንድነዉ የታገለዉ ቆይ 🙄?
የመኪና. …ተሰጠው?!
Meches Nuron nw mitagelew …tagelo sishenef shelemut
ሬድዋን ሁሴን ነው 🚶♂️🚶♂️
ላማሜ ሲያንሰው ነው
የማንነት ታጋይ ማለት 🙄
ይህ ሰው ለሰራው ስራ የንሰዋል እንጂ የሚየውቅ ያውቀዋል ለሰጪው አላህ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥልን
የሙዚቃው ንጉስ …
Waw yigebawal