0
#FastMereja I ዛሬ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም የንቦች ቀን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ የሚገኘው “ጫካ ማር” ሰራተኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም አከናውኗል።
አቶ መንግስቱ የኋላው የጫካ ማር ማናጀር ባደረጉት ንግግር ጫካ ማር ከ70 አመት በላይ በስራው ላይ ቆይቷል በሁሉም ክልሎች እንገኛለን ዛሬ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በጅማ የንቦች ቀንን አክብረናል፣ ከ15 አይነት በላይ የማር ቃና አይነቶችን ለገበያ በማቅረብ በርካታ ደንበኞችን ያፈራ አንጋፋ ድርጅት ነው ብሏል።
የማር ጥራቱ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በሚሸጡት እያንዳንዱ ማሮች ላይ ባርኮድ በማስቀመጥ ለሚመጣ ቅሬታ እስከ ታች ድረስ የሚመረመርበት አሰራር መዘርጋታቸውን አቶ መንግስቱ ተናግሯል።
በተጨማሪም ጫካ ማር በደም አይነት እየጠየቅን የሚስማማውን የማር አይነት እየሸጡ እንደሆነም ገልጿል።
ጫካ ማር በአዲስ አበባ ሁለት ቅርጫፎች ሲኖሩት በአሜሪካ በኤጀንት በኩል እንደሚሸጥ ገልጿል። ለአዲስ አበባ ደንበኞች የነፃ ዴሊቨሪ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሯል።





1 comment
ዛሬ ለፓርላማ የቀረበው በኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ክርክር አሰነስቷል። የፓርላማው አባላት እንደ ደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓት: የሀገሬው ዜጋ የማይደርሱበት የከተማ ክፍል ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
~ ካዛንቺስ የኢማራት ሰዎች ብቻ ሆና: ቦሌ የቻይኖች ብቻ ሆና ልናይ እንችላለን። ኢትዮጵያዊ ተቀጥሮ ካልሆነ በስተቀር: በአይኑም ማየት የማይችል መንደር ማለት ነው።