0
#FastMereja I ንጋት በጎ አድራጎት ተራድኦ ድርጅት ከግንቦት 16-20/2017 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ዛሬ በቫምዳስ ሲኒማ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ በቲክቶክ እና በዩቲዩብ በቀጥታ ስርጭት ለአራት ቀናት በተከታታይ እንደሚካሄድ ተነግሯል።
በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይም የቀራፂ እና ሰዓሊ ግሩም ስራዎች በጨረታ እንደሚሸጡ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
ንጋት በጎ አድራጎት ተራድኦ ድርጅት በአቶ ንጋቱ አስፋ የተመሰረተ ሲሆን ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ መስራት ከጀመረ 8 ወራት አስቆጥሯክ አሁን ላይ 84 ዜጎችን ከጎዳና በማንሳት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።




