banner

የአፍሪካ ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

#FastMereja I ”ለባህል ዘርፉ የመንግስት ድጋፍ ስላለው ጠቃሚነት የፖሊሲ ውይይት” በተሰኘ ርዕስ ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ኩነቶች እየተካሄደ ይገኛል።

መረኀ ግብሩ በፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአለ ፈለገ ሰላም የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት እየተካሄደ ሲሆን በመቀጠልም ከሰዓት በመቀጠል እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ በአራት ኪሎ ፕላዛ ሰርከስ፣ ሙዚቃ እና ኪነ-ጥበብ የሚቀርቡበት ደማቅ ዝግጅት እንደሚኖር ተነግሯል።

“የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ለትውልደ አፍሪካውያን” በሚል ርዕስ የሚከበረው የዘንድሮው የአፍሪካ ቀን፤ ውይይትን ማዳበር፣ በፍትህ፣ ፍትሃዊነት እና የባህል ተሃድሶ ረገድ የሚተገበሩ ተግባራትን ለማሳደግ ያልማል የተባለ ሲሆን ኪነ-ጥበባዊ ገላጮችን ከቅስቀሳ ጋር በማዋሃድ ክብረ-በዓሉ ባህል ለህብረተሰብ አንድነት እንዲሁም ልማት ያለውን ዋና ሚና አጉልቶ ያሳያል ተብሏል።

“ህብረት ጥንካሬን ይሰጣል ለዚህም ነው አራቱ የሞያ ማኅበራት በጋራ በመሆን የአፍሪካ ቀንን የሚያከብሩት። በኪነ-ጥበብ ውስጥ በጋራ መሰባሰብ በሰዎች ዘንድ አንድነትን ይፈጥራል እንዲሁም ዘርፉን ያሳድጋል፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማኅበራት ህብረት ክቡር ዶክተር ዳዊት ይፍሩ ተናግረዋል፡፡

ሰላም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንን አስመልክቶ በኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ (ሲኤፍሲኤ) ፕሮጀክት አማካይነት ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማኅበራት ህብረት፣ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፅያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ማኅበር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ድጋፍ እንደተዘጋጀ ተጠቅሷል።




1 comment

Um Abrsh King May 24, 2025 - 9:38 am

ማናት ደሞ አፍሪካ

Reply

Leave a Comment