banner

7ኛው አግሮፉድ እና ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

#FastMereja I ከ14 ሀገራት የተውጣጡ ከ140 በላይ አውደ ርዕይ አቅራቢዎች ለኢትዮጵያ ገበያ የሚስማሙ ምርቶችን እና መፍትሄዎችን ያቀርባሉ፡፡

በጀርመኑ ፌርትሬድ መሴ (fairtrade Messe) እና በኢትዮጰያ አጋሩ ፕራና ኢቨንትስ (Prana Events) ትብብር የሚዘጋጀው አግሮፉድ እና ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ ለ7ኛ ጊዜ የዘርፉ ተዋንያንን ከመላው ዓለም አሰባስቦ ከሰኔ 12-14 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

የዘንድሮ ኹነት ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ140 በላይ አቅራቢዎች ለኢትዮጵያ ገበያ ተብለው የተዘጋጁ ምርቶችን እና መፍትሄዎችን ያቀርባሉ።

ኹነቱ ዘመኑ ያፈራቸውን ምርቶችና መፍትሄዎች ለሚፈልጉ ከንግዱም ሆነ ከመንግስት አካላት የተውጣጡ ውሳኔ ሰጪዎችን የሚስብ ኹነት ነው ተብሏል።

በጠንካራ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በአንዲስትሪ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የመጠጥ አምራቾች ማህበር በተዘጋጁት የውይይት መድረኮች ላይ በመሳተፍ አዳዲስ መረጃዎችን እና እውቀትን ለመሸመት የሚያስችል ልዩ አጋጣሚን እንደሚፈጥር ተነግሯል።

በ2025 አዲስ የተካተተው የኢትዮጵያ የምግብ ንግድ ትርዒት ከአግሮፉድ ኢትዮጵያ ጋር ጎን ለጎን የሚካሄድ ሲሆን፣ በምግብ እና መጠጥ ምርቶች ላይ ትኩረት ያደረግ ኹነት ነው፡፡ በተጨማሪም ኢትዮፒካ የቡና ንግድ ትርዒት ከአግሮፉድ ኢትዮጵያ ጋር ጎን ለጎን የሚካሄድ ይሆናል።

እ.ኤ.አ. በ1991 የተመሰረተው ፌር ትሬድ (fairtrade) በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ለረጅም ጊዜ ግንባርቀደም ከሆኑ የግብርና ምግብ (agrofood) እና ፕላስትፕሪንትፓክ (plastprintpack) ሙያዊ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች አዘጋጆች አንዱ ነው።

ፕራና ኢቨንትስ በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ትላልቅና ዓለም አቀፍ ኤክስፖዎችንና ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት ከሚጠቀሱ ስመጥር ኩባንያዎች አንዱ ነው።





1 comment

Anes Geberil June 3, 2025 - 10:35 am

አዬ ፈጣሪ

Reply

Leave a Comment