banner

ወደ ውጪ ሀገር የሚላኩ የላብራቶሪ ምርመራን በሀገር ውስጥ ማድረግ የሚያስችል የላብራቶሪ ማሽን ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል አስገ

ወደ ውጪ ሀገር የሚላኩ የላብራቶሪ ምርመራን በሀገር ውስጥ ማድረግ የሚያስችል የላብራቶሪ ማሽን ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል አስገባ

#FastMereja I በኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራ የጀመረው ይኸው Mindray BS-680M’ (intergrated)
የተሰኘው ማሽን በምሥራቅ አፍሪካ 2ኛ፤ በኢትዮጵያ በግል የሕክምና ተቋማት የመጀመሪያ ያደርገዋል።

የኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃን ተድላ፣ ይህንን ዘመናዊ ማሽን የማስገባት ዓላማቸው ለህብረተሰቡ የተሻለና ጥራቱ የተረጋገጠ የህክምና አገልግሎት መስጠት መሆኑን ገልጸዋል። የማሽኑ ሥራ መጀመር ለላብራቶሪ ቴስት ወደውጪ ሀገር የሚደረግ ጉዞን በማስቀረት ለሀገር የውጪ ምንዛሪ የማዳን ሚና ይጫወታል ብለዋል።

‘Mindray BS-680M (intergrated)
የላብራቶሪ ማሽን በሰዓት ከ840 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የህክምና ምርመራዎችን የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን፣ ከሰው ንክኪ የጸዳ በመሆኑ የውጤቶችን ትክክለኛነት በእጅጉ ይጨምራል። ይህ ባህሪ የምርመራ ሂደቶችን ፍጥነት ከማሳደጉም በላይ የውጤቶችን አስተማማኝነት በማረጋገጥ ለታካሚዎች ትክክለኛ የህክምና ክትትል እንዲያገኙ ያስችላል።

የማይንድሬይ የምስራቅ አፍሪካ የሴልስ ማናጀር የሆኑት ዊልያም ፌኔል በበኩላቸው፣ ማይንድሬይ በዓለም ላይ ለህክምና ተቋማት በርካታ የህክምና መሳሪያዎችን በጥናት ላይ በተመሰረተ መልኩ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ኩባንያው ለጥናትና ምርምር ብቻ 500 ሚሊዮን ዶላር መድቦ እየሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ሚስተር ዳይላን የኩባንያው የምርት ሽያጭ ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው ይህ ማሽን የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቶችን ስህተቶች በመቀነስ እና በአነስተኛ የሰው ኃይል ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳለው አስረድተዋል።

የጊላንዶ ባዮሜድካል ሶሉሽን መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ይዲዲያ ስለሺ ባለፉት 10 ዓመታት የህክምና መሳሪያዎችን ጥገና ሲሰሩ መቆየታቸውን እና ባለፉት አምስት ዓመታት ደግሞ በርካታ የህክምና መሳሪያዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የሆስፒታሉ የላብራቶሪ ክፍል ኃላፊ አቶ ደሳለኝ መርጊያው፣ ሆስፒታሉ ገና ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጸው፣ ለሆስፒታሉ ባለቤት ለአቶ ብርሃን ተድላ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ አዲስ ማሽን የሆስፒታሉን የላብራቶሪ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ስዮም ካሳም በበኩላቸው በማሽኑ መምጣት ከፍተኛ ደስታቸውን እና ለታካሚዎች በሚሰጠው አገልግሎት ላይ የሚያመጣውን አዎንታዊ ለውጥ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ላብራቶሪ በቅርቡ ከኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የጥራት ሰርተፊኬት ማግኘቱን መዘገባችን ይታወሳል።





Leave a Comment