banner

ዝነኛው ሳምሪ ሞካሽ የባህል አልባሳት ሁለተኛ ቅርንጫፉን ከፈተ

#FastMereja I ሳምሪ ሞካሽ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በአዲስ አበባ በዛሬው እለት በይፋ ከፈተ።

በተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛ ቅርንጫፉን የከፈተው ሳምሪ ሞካሽ የፋሽን እንዲስትሪው ላይ ፈጠራ የታከለበት ስራ እየሠራ እንደሚገኝ የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሳምራዊት መሀመድ በምረቃው ስነስርዓት ላይ ተናግሯል።

በቀጣይ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ክልሎች እና ከኢትዮጵያ ውጪ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ማቀዳቸውን ገልጸዋል።

ዛሬ በይፋ የተከፈተው ሁለተኛው ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ አደይ አበባ ስታድየም ሴንተር አዲስ ህንፃ ላይ መገኛውን አድርጓል። ሳምሪ ሞካሽ ከ30 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር ችሏል።

የሁለተኛው ቅርንጫፍ ምረቃ መርሃግብር ላይ ታዋቂ ድምፃዊያን፣ የፊልም ተዋንያን፣ የማስታወቂያ ባለሙያዎችና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተውበታል።

#ቢዝነስ





Leave a Comment