0
#FastMereja I ከአመታት በፊት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን በማግኘት በርካታ ተጠቃሚ ያገኘው ቲክቶክ ቁጥር አንድ የባለጌ መነኻሪያ ሆኗል።
ማንኛውም ግለሰብ እየተነሳ ብሄር ይሳደባል፣ ኃይማኖት ያንቋሽሻል ህዝቡም ይከተለዋል በሰራው መጥፎ ስራ ዝነኛ ይሆናል።
እንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ በብዛት የሚሳተፉት ወጣት የሚባሉ ታዳጊዎች ሳይሆኑ ጎልማሳ የሚባሉ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች ናቸው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በወጣት ቲክቶከሮች ላይ እርምጃ እየተወሰደ በተለያየ ጊዜ መረጃ እንሰማለን እነዚህ ወጣት ቲክቶከሮች ከጥፋታቸው ተምረው ይቅርታም ሲጠይቁ እንመለከታለን።
ግን ግን…
ህጉ ጎልማሶች ላይ እየተሽኮረመመ ይመስላል። ብሄር፣ ኃይማኖት የሚሳደቡ ግለሰቦች ያለ ከልካይ ከባህር ማዶ ኢትዮጵያ መጥተው ጀብድ እንደሰራ ሰው ደረታቸውን ነፍተው የተመለሱ እዚህም የሚኖሩ አሉ ህጉ እነሱን እየነካ አይደለም ትኩረት ይሰጠው።
ማንም ሰው ከህግ በላይ አይደለም!


4 comments
ቲክቶክ ካልተዘጋ አብይ በቅርቡ ይዘጋል
Right
ባልና ሚስት ከአንድ ኩሬ ይቀዳሉ😍
Tiktoker neh ende?